1 |
ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ፤ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ። |
2 |
ከሦስት ቀንም በኋላ አለቆች በሰፈሩ መካከል አለፉ። |
3 |
ሕዝቡን። የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦትና ሌዋውያን ካህናት ተሸክመውት ባያችሁ ጊዜ፥ ከሰፈራችሁ ተነስታችሁ ተከተሉት። |
4 |
በእናንተና በታቦቱ መካከል ያለው ርቀት በስፍር ሁለት ሺህ ክንድ ያህል ይሁን፤ በዚህ መንገድ በፊት አልሄዳችሁበትምና የምትሄዱበትን መንገድ እንድታውቁ ወደ ታቦቱ አትቅረቡ ብለው አዘዙ። |
5 |
ኢያሱም ሕዝቡን። ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ አለ። |
6 |
ኢያሱም ካህናቱን። የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ ብሎ ተናገራቸው፤ የቃል ኪዳኑንም ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ። |
7 |
እግዚአብሔርም ኢያሱን። ከሙሴ ጋር እንደ ሆንሁ እንዲሁ ከአንተ ጋር መሆኔን ያውቁ ዘንድ በዚህ ቀን በእስራኤል ሁሉ ዓይን ከፍ ከፍ አደርግህ ዘንድ እጀምራለሁ። |
8 |
አንተም የቃል ኪዳኑን ታቦት የሚሸከሙትን ካህናት። በዮርዳኖስ ውኃ ዳር ስትደርሱ በዮርዳኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ አለው። |
9 |
ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች። ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አለ። |
10 |
ኢያሱም አለ። ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈጽሞ እንዲያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ። |
11 |
እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል። |
12 |
አሁንም ከእስራኤል ነገዶች አሥራ ሁለት ሰዎች ምረጡ፤ ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው ይሁን። |
13 |
እንዲህም ይሆናል፤ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፤ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል። |
14 |
እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር። |
15 |
እንደ መከር ወራት ሁሉ ዮርዳኖስ እጅግ ሞልቶ ነበርና ታቦት ተሸካሚዎቹ ወደ ዮርዳኖስ ሲደርሱ፥ ታቦቱንም የተሸከሙት የካህናቱ እግሮች በውኃው ዳር ሲጠልቁ፥ |
16 |
ከላይ የሚወርደው ውኃ ቆመ፤ በጻርታን አጠገብ ባለችው አዳም በምትባል ከተማ በሩቅ ቆሞ በአንድ ክምር ተነሣ፤ ወደ ዓረባ ባሕር ወደ ጨው ባሕር የሚወርደው ውኃ ፈጽሞ ተቋረጠ፤ ሕዝቡም በኢያሪኮ ፊት ለፊት ተሻገሩ። |
17 |
የእግዚአብሔርንም የቃል ኪዳን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በዮርዳኖስ መካከል በደረቅ መሬት ጸንተው ቆመው ነበር፥ ሕዝቡም ሁሉ ዮርዳኖስን ፈጽመው እስኪሻገሩ ድረስ እስራኤል ሁሉ በደረቅ መሬት ተሻገሩ።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ኢያሱ 3:1 |
ኢያሱ 3:2 |
ኢያሱ 3:3 |
ኢያሱ 3:4 |
ኢያሱ 3:5 |
ኢያሱ 3:6 |
ኢያሱ 3:7 |
ኢያሱ 3:8 |
ኢያሱ 3:9 |
ኢያሱ 3:10 |
ኢያሱ 3:11 |
ኢያሱ 3:12 |
ኢያሱ 3:13 |
ኢያሱ 3:14 |
ኢያሱ 3:15 |
ኢያሱ 3:16 |
ኢያሱ 3:17 |
|
|
|
|
|
|
ኢያሱ 1 / ኢያሱ 1 |
ኢያሱ 2 / ኢያሱ 2 |
ኢያሱ 3 / ኢያሱ 3 |
ኢያሱ 4 / ኢያሱ 4 |
ኢያሱ 5 / ኢያሱ 5 |
ኢያሱ 6 / ኢያሱ 6 |
ኢያሱ 7 / ኢያሱ 7 |
ኢያሱ 8 / ኢያሱ 8 |
ኢያሱ 9 / ኢያሱ 9 |
ኢያሱ 10 / ኢያሱ 10 |
ኢያሱ 11 / ኢያሱ 11 |
ኢያሱ 12 / ኢያሱ 12 |
ኢያሱ 13 / ኢያሱ 13 |
ኢያሱ 14 / ኢያሱ 14 |
ኢያሱ 15 / ኢያሱ 15 |
ኢያሱ 16 / ኢያሱ 16 |
ኢያሱ 17 / ኢያሱ 17 |
ኢያሱ 18 / ኢያሱ 18 |
ኢያሱ 19 / ኢያሱ 19 |
ኢያሱ 20 / ኢያሱ 20 |
ኢያሱ 21 / ኢያሱ 21 |
ኢያሱ 22 / ኢያሱ 22 |
ኢያሱ 23 / ኢያሱ 23 |
ኢያሱ 24 / ኢያሱ 24 |