1 |
የእስራኤልም ልጆች ጕዞ ከሙሴና ከአሮን እጅ በታች በጭፍሮቻቸው ከግብፅ በወጡ ጊዜ እንዲህ ነበረ። |
2 |
ሙሴም በእግዚአብሔር ትእዛዝ እንደ ጕዞአቸው አወጣጣቸውን ጻፈ፤ እንደ አወጣጣቸውም ጕዞአቸው እንዲህ ነበረ። |
3 |
በመጀመሪያው ወር ከወሩም በአሥራ አምስተኛው ቀን ከራምሴ ተጓዙ፤ ከፋሲካ በኋላ በነጋው የእስራኤል ልጆች ግብፃውያን ሁሉ እያዩ ከፍ ባለች እጅ ወጡ። |
4 |
በዚያም ጊዜ ግብፃውያን እግዚአብሔር የገደላቸውን በኵሮቻቸውን ይቀብሩ ነበር፤ በአማልክቶቻቸውም ደግሞ እግዚአብሔር ፈረደባቸው። |
5 |
የእስራኤልም ልጆች ከራምሴ ተጕዘው በሱኮት ሰፈሩ። |
6 |
ከሱኮትም ተጕዘው በምድረ በዳ ዳርቻ ባለች በኤታም ሰፈሩ። |
7 |
ከኤታምም ተጕዘው በበኣልዛፎን ፊት ወደ ነበረች ወደ ፊሀሒሮት ተመለሱ፤ በሚግዶልም ፊት ለፊት ሰፈሩ። |
8 |
ከፊሀሒሮትም ተጕዘው በባሕሩ ውስጥ ወደ ምድረ በዳ አለፉ፤ በኤታምም በረሀ የሦስት ቀን መንገድ ሄደው በማራ ሰፈሩ። |
9 |
ከማራም ተጕዘው ወደ ኤሊም መጡ፤ በኤሊምም አሥራ ሁለት የውኃ ምንጮች ሰባ ዘንባቦችም ነበሩ፤ በዚያም ሰፈሩ። |
10 |
ከኤሊምም ተጕዘው በኤርትራ ባሕር ዳር ሰፈሩ። |
11 |
ከኤርትራም ባሕር ተጕዘው በሲን ምድረ በዳ ሰፈሩ። |
12 |
ከሲን ምድረ በዳም ተጕዘው በራፋቃ ሰፈሩ። |
13 |
ከራፋቃም ተጕዘው በኤሉስ ሰፈሩ። |
14 |
ከኤሉስም ተጕዘው በራፊዲም ሰፈሩ፤ በዚያም ሕዝቡ የሚጠጡት ውኃ አልነበረም። |
15 |
ከራፊዲምም ተጕዘው በሲና ምድረ በዳ ሰፈሩ። |
16 |
ከሲናም ምድረ በዳ ተጕዘው በምኞት መቃብር ሰፈሩ። |
17 |
ከምኞት መቃብርም ተጕዘው በሐጼሮት ሰፈሩ። |
18 |
ከሐጼሮትም ተጕዘው በሪትማ ሰፈሩ። |
19 |
ከሪትማም ተጕዘው በሬሞን ዘፋሬስ ሰፈሩ። |
20 |
ከሬሞን ዘፋሬስም ተጕዘው በልብና ሰፈሩ። |
21 |
ከልብናም ተጕዘው በሪሳ ሰፈሩ። |
22 |
ከሪሳም ተጕዘው በቀሄላታ ሰፈሩ። |
23 |
ከቀሄላታም ተጕዘው በሻፍር ተራራ ሰፈሩ። |
24 |
ከሻፍር ተራራም ተጕዘው በሐራዳ ሰፈሩ። |
25 |
ከሐራዳም ተጕዘው በመቅሄሎት ሰፈሩ። |
26 |
ከመቅሄሎትም ተጕዘው በታሐት ሰፈሩ። |
27 |
ከታሐትም ተጕዘው በታራ ሰፈሩ። |
28 |
ከታራም ተጕዘው በሚትቃ ሰፈሩ። |
29 |
ከሚትቃም ተጕዘው በሐሽሞና ሰፈሩ። |
30 |
ከሐሽሞናም ተጕዘው በሞሴሮት ሰፈሩ። |
31 |
ከሞሴሮትም ተጕዘው በብኔያዕቃን ሰፈሩ። |
32 |
ከብኔያዕቃንም ተጕዘው በሖርሃጊድጋድ ሰፈሩ። |
33 |
ከሖርሃጊድጋድም ተጕዘው በዮጥባታ ሰፈሩ። |
34 |
ከዮጥባታም ተጕዘው በዔብሮና ሰፈሩ። |
35 |
ከዔብሮናም ተጕዘው በዔጽዮንጋብር ሰፈሩ። |
36 |
ከዔጽዮንጋብርም ተጕዘው በጺን ምድረ በዳ ሰፈሩ፤ ይህችም ቃዴስ ናት። |
37 |
ከቃዴስም ተጕዘው በኤዶምያስ ምድር ዳርቻ ባለው በሖር ተራራ ሰፈሩ። |
38 |
ካህኑም አሮን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሖር ተራራ ላይ ወጣ፥ በዚያም የእስራኤል ልጆች ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ በአርባኛው ዓመት በአምስተኛው ወር ከወሩም በመጀመሪያው ቀን ሞተ። |
39 |
አሮንም በሖር ተራራ በሞተ ጊዜ ዕድሜው መቶ ሀያ ሦስት ዓመት ነበር። |
40 |
በከነዓን ምድርም በደቡብ በኩል ተቀምጦ የነበረው ከነዓናዊው የዓራድ ንጉሥ የእስራኤል ልጆች እንደ መጡ ሰማ። |
41 |
እነርሱም ከሖር ተራራ ተጕዘው በሴልሞና ሰፈሩ። |
42 |
ከሴልሞናም ተጕዘው በፉኖን ሰፈሩ። |
43 |
ከፉኖንም ተጕዘው በኦቦት ሰፈሩ። |
44 |
ከኦቦትም ተጕዘው በሞዓብ ዳርቻ ባለው በጋይ ሰፈሩ። |
45 |
ከጋይም ተጕዘው በዲቦንጋድ ሰፈሩ። |
46 |
ከዲቦንጋድም ተጕዘው በዓልሞንዲብላታይም ሰፈሩ። |
47 |
ከዓልሞንዲብላታይምም ተጕዘው በናባው ፊት ባሉ በዓብሪም ተራሮች ላይ ሰፈሩ። |
48 |
ከዓብሪምም ተራሮች ተጕዘው በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ባለው በሞዓብ ሜዳ ላይ ሰፈሩ። |
49 |
በዮርዳኖስም አጠገብ በሞዓብ ሜዳ ላይ ከቤትየሺሞት እስከ አቤልሰጢም ድረስ ሰፈሩ። |
50 |
እግዚአብሔርም ሙሴን በዮርዳኖስ አጠገብ በኢያሪኮ ፊት ለፊት በሞዓብ ሜዳ ላይ እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
51 |
ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው። ወደከነዓን ምድር ዮርዳኖስን በተሻገራችሁ ጊዜ፥ |
52 |
የአገሩን ሰዎች ሁሉ ከፊታችሁ ታሳድዳላችሁ፥ የተቀረጹትንም ድንጋዮቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ ቀልጠው የተሠሩትንም ምስሎቻቸውን ሁሉ ታጠፋላችሁ፥ በኮረብታ ላይ ያሉትን መስገጃዎቻቸውንም ታፈርሳላችሁ፤ |
53 |
ምድሪቱንም ለእናንተ ርስት አድርጌ ሰጥቼአችኋለሁና ምድሪቱን ትወርሱአታላችሁ ትቀመጡባታላችሁም። |
54 |
ምድሪቱንም በየወገኖቻችሁ በዕጣ ትወርሳላችሁ፤ ለብዙዎች እንደ ብዛታቸው ለጥቂቶቹም እንደ ጥቂትነታቸው መጠን ርስትን ትሰጣላችሁ፤ እያዳንዱ ሁሉ ዕጣ እንደ ወደቀለት በዚያ ርስቱ ይሆናል፤ በየአባቶቻችሁ ነገዶች ትወርሳላችሁ። |
55 |
የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ እሾህ ለጎናችሁም እንደሚወጋ ነገር ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል። |
56 |
እኔም በእነርሱ አደርገው ዘንድ ያሰብሁትን በእናንተ አደርግባችኋለሁ።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |