1 |
በለዓምም እግዚአብሔር እስራኤልን ይባርክ ዘንድ እንዲወድድ ባየ ጊዜ፥ አስቀድሞ ያደርግ የነበረውን አስማት ይሻ ዘንድ አልሄደም፤ ነገር ግን ወደ ምድረ በዳ ፊቱን አቀና። |
2 |
በለዓምም ዓይኑን አንሥቶ እስራኤል በየነገዱ ተቀምጦ አየ፤ የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ መጣ። |
3 |
ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ። የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹ የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤ |
4 |
የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል። |
5 |
ያዕቆብ ሆይ፥ ድንኳኖችህ፥ እስራኤል ሆይ ማደሪያዎችህ ምንኛ ያምራሉ! |
6 |
እንደ ሸለቆች፥ በወንዝ ዳር እንዳሉ አትክልቶች፥ እግዚአብሔር እንደ ተከለው እሬት በውኃም ዳር እንዳሉ ዝግባዎች ተዘርግተዋል። |
7 |
ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል። |
8 |
እግዚአብሔርም ከግብፅ አውጥቶታል፤ ጕልበቱ አንድ ቀንድ እንዳለው ነው፤ ጠላቶቹን አሕዛብን ይበላል፥ አጥንቶቻቸውንም ይሰባብራል፥ በፍላጾቹም ይወጋቸዋል። |
9 |
እንደ አንበሳ ዐርፎ ተኝቶአል፥ እንደ እንስቲቱም አንበሳ ተጋድሞአል፤ ማን ያስነሣዋል? የሚመርቅህ ሁሉ የተመረቀ ይሁን፥ የሚረግምህም ሁሉ የተገመ ይሁን። |
10 |
የባላቅም ቍጣ በበለዓም ላይ ነደደ፤ እጆቹንም አጨበጨበ፤ ባላቅም በለዓምን። ጠላቶቼን ትረግም ዘንድ ጠራሁህ፥ እነሆም፥ ሦስት ጊዜ ፈጽመህ መረቅሃቸው፤ አሁንም እንግዲህ ወደ ስፍራህ ሽሽ፤ |
11 |
እኔ አከብርህ ዘንድ ወድጄ ነበር፤ እግዚአብሔር ግን፥ እነሆ፥ ክብርህን ከለከለ አለው። |
12 |
በለዓምም ባላቅን አለው። ባላቅ በቤቱ የሞላውን ብርና ወርቅ ቢሰጠኝ፥ መልካሙን ወይም ክፉውን ከልቤ ለማድረግ የእግዚአብሔርን ቃል እተላለፍ ዘንድ አይቻለኝም፤ እግዚአብሔር የተናገረውን እርሱን እናገራለሁ ብዬ ወደ እኔ ለላክሃቸው መልእክተኞች አልተናገርኋቸውምን? |
13 |
*** |
14 |
አሁንም፥ እነሆ፥ ወደ ሕዝቤ እሄዳለሁ፤ ና፥ ይህ ሕዝብ በኋለኛው ዘመን በሕዝብህ ላይ የሚያደርገውን እነግርሃለሁ። |
15 |
ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ። የቢዖር ልጅ በለዓም እንዲህ ይላል፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት ሰው እንዲህ ይላል፤ |
16 |
የእግዚአብሔርን ቃል የሚሰማ፥ የልዑልንም እውቀት የሚያውቅ፥ ሁሉን የሚችል የአምላክን ራእይ የሚያይ፥ የወደቀው፥ ዓይኖቹም የተከፈቱለት እንዲህ ይላል። |
17 |
አየዋለሁ፥ አሁን ግን አይደለም፤ እመለከተዋለሁ፥ በቅርብ ግን አይደለም፤ ከያዕቆብ ኮከብ ይወጣል፥ ከእስራኤል በትር ይነሣል፥ የሞዓብንም ማዕዘኖች ይመታል፥ የሤትንም ልጆች ያጠፋል። |
18 |
ኤዶምያስም ርስቱ ይሆናል፥ ጠላቱ ሴይር ደግሞ ርስቱ ይሆናል፤ እስራኤልም በኃይል ያደርጋል። |
19 |
ከያዕቆብም የሚወጣ ገዥ ይሆናል፥ ከከተማውም የቀሩትን ያጠፋል። |
20 |
አማሌቅንም አይቶ ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ። አማሌቅ የአሕዛብ አለቃ ነበረ፤ ፍጻሜው ግን ወደ ጥፋት ይመጣል። |
21 |
ቄናውያንንም አይቶ ምሳሌውን ይምስል ጀመር፥ እንዲህም አለ። ማደሪያህ የጸና ነው፥ ጎጆህም በአምባ ላይ ተሠርቶአል፤ |
22 |
ነገር ግን አሦር እስኪማርክህ ድረስ ቄናዊው ለጥፋት ይሆናል። |
23 |
ምሳሌውንም ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ። እግዚአብሔር ይህን ሲያደርግ አወይ! ማን በሕይወት ይኖራል? |
24 |
ከኪቲም ዳርቻ መርከቦች ይመጣሉ፥ አሦርንም ያስጨንቃሉ፥ ዔቦርንም ያስጨንቃሉ፤ እርሱም ደግሞ ወደ ጥፋት ይመጣል። |
25 |
በለዓምም ተነሣ፥ ተመልሶም ወደ ስፍራው ሄደ፤ ባላቅም ደግሞ መንገዱን ሄደ።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ቁጥሮች 24:1 |
ቁጥሮች 24:2 |
ቁጥሮች 24:3 |
ቁጥሮች 24:4 |
ቁጥሮች 24:5 |
ቁጥሮች 24:6 |
ቁጥሮች 24:7 |
ቁጥሮች 24:8 |
ቁጥሮች 24:9 |
ቁጥሮች 24:10 |
ቁጥሮች 24:11 |
ቁጥሮች 24:12 |
ቁጥሮች 24:13 |
ቁጥሮች 24:14 |
ቁጥሮች 24:15 |
ቁጥሮች 24:16 |
ቁጥሮች 24:17 |
ቁጥሮች 24:18 |
ቁጥሮች 24:19 |
ቁጥሮች 24:20 |
ቁጥሮች 24:21 |
ቁጥሮች 24:22 |
ቁጥሮች 24:23 |
ቁጥሮች 24:24 |
ቁጥሮች 24:25 |
|
|
|
|
|
|
ቁጥሮች 1 / ቁጥሮች 1 |
ቁጥሮች 2 / ቁጥሮች 2 |
ቁጥሮች 3 / ቁጥሮች 3 |
ቁጥሮች 4 / ቁጥሮች 4 |
ቁጥሮች 5 / ቁጥሮች 5 |
ቁጥሮች 6 / ቁጥሮች 6 |
ቁጥሮች 7 / ቁጥሮች 7 |
ቁጥሮች 8 / ቁጥሮች 8 |
ቁጥሮች 9 / ቁጥሮች 9 |
ቁጥሮች 10 / ቁጥሮች 10 |
ቁጥሮች 11 / ቁጥሮች 11 |
ቁጥሮች 12 / ቁጥሮች 12 |
ቁጥሮች 13 / ቁጥሮች 13 |
ቁጥሮች 14 / ቁጥሮች 14 |
ቁጥሮች 15 / ቁጥሮች 15 |
ቁጥሮች 16 / ቁጥሮች 16 |
ቁጥሮች 17 / ቁጥሮች 17 |
ቁጥሮች 18 / ቁጥሮች 18 |
ቁጥሮች 19 / ቁጥሮች 19 |
ቁጥሮች 20 / ቁጥሮች 20 |
ቁጥሮች 21 / ቁጥሮች 21 |
ቁጥሮች 22 / ቁጥሮች 22 |
ቁጥሮች 23 / ቁጥሮች 23 |
ቁጥሮች 24 / ቁጥሮች 24 |
ቁጥሮች 25 / ቁጥሮች 25 |
ቁጥሮች 26 / ቁጥሮች 26 |
ቁጥሮች 27 / ቁጥሮች 27 |
ቁጥሮች 28 / ቁጥሮች 28 |
ቁጥሮች 29 / ቁጥሮች 29 |
ቁጥሮች 30 / ቁጥሮች 30 |
ቁጥሮች 31 / ቁጥሮች 31 |
ቁጥሮች 32 / ቁጥሮች 32 |
ቁጥሮች 33 / ቁጥሮች 33 |
ቁጥሮች 34 / ቁጥሮች 34 |
ቁጥሮች 35 / ቁጥሮች 35 |
ቁጥሮች 36 / ቁጥሮች 36 |