1 |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
2 |
አሮንን፥ ከእርሱም ጋር ልጆቹን፥ ልብሱንም፥ የቅብዓቱንም ዘይት፥ ለኃጢአት መሥዋዕትም የሆነውን ወይፈን፥ ሁለቱንም አውራ በጎች፥ የቂጣውንም እንጀራ ሌማት ውሰድ፤ |
3 |
ማኅበሩንም ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሰብስባቸው። |
4 |
ሙሴም እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ማኅበሩ ሁሉ ወደ መገናኛው ድንኳን ደጃፍ ተሰበሰቡ። |
5 |
ሙሴም ማኅበሩን። እግዚአብሔር ይደረግ ዘንድ ያዘዘው ነገር ይህ ነው አላቸው። |
6 |
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አቀረበ፥ በውኃም አጠባቸው። |
7 |
ሸሚዝም አለበሰው፥ በመታጠቂያም አስታጠቀው፥ ቀሚስም አለበሰው፥ ኤፉድም ደረበለት፥ በብልሃትም በተጠለፈ ቋድ አስታጠቀውና በእርሱ ላይ አሰረው። |
8 |
የደረት ኪስ በእርሱ ላይ አደረገ፤ በደረቱ ኪስም ውስጥ ኡሪምንና ቱሚምን አኖረበት። |
9 |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው በራሱ ላይ መጠምጠሚያውን አደረገ፤ በመጠምጠሚያውም ላይ በፊቱ በኩል የተቀደሰውን አክሊል፥ ቅጠል የሚመስለውን የወርቅ ምልክት፥ አደረገ። |
10 |
ሙሴም የቅብዓቱን ዘይት ወሰደ፥ ማደሪያውንና በውስጡ ያለውን ሁሉ ቀብቶ ቀደሳቸው። |
11 |
ከእርሱም በመሠዊያው ላይ ሰባት ጊዜ ረጨ፤ ይቀድሳቸውም ዘንድ መሠዊያውንና ዕቃውን ሁሉ፥ የመታጠቢያውን ሰንና መቀመጫውን ቀባ። |
12 |
ከቅብዓቱም ዘይት በአሮን ራስ ላይ አፈሰሰ፥ ይቀድሰውም ዘንድ ቀባው። |
13 |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፥ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፥ በመታጠቂያም አስታጠቃቸው፥ ቆብም ደፋባቸው። |
14 |
የኃጢአትንም መሥዋዕት ወይፈን አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በኃጢአቱ መሥዋዕት ወይፈን ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። |
15 |
አረደውም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፥ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፥ ያስተሰርይለትም ዘንድ ቀደሰው። |
16 |
በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ የጕበቱንም መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች ስባቸውንም ወሰደ፤ ሙሴም በመሠዊያው ላይ አቃጠለው። |
17 |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ወይፈኑን፥ ቁርበቱንም፥ ሥጋውንም፥ ፈርሱንም ከሰፈሩ ውጭ በእሳት አቃጠለ። |
18 |
ለሚቃጠል መሥዋዕትም የሚሆን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። |
19 |
አረደውም፤ ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨው። |
20 |
አውራውንም በግ በየብልቱ ቈረጠ፤ ሙሴም ጭንቅላቱን ብልቶቹንም ስቡንም አቃጠለ። |
21 |
የሆድ ዕቃውንና እግሮቹንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አውራውን በግ ሁሉ በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤ ይህ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ለእግዚአብሔር የእሳት ቍርባን ነበረ። |
22 |
ለቅድስናም የሚሆነውን ሁለተኛውን አውራ በግ አቀረበ፤ አሮንና ልጆቹም በአውራው በግ ራስ ላይ እጆቻቸውን ጫኑ። |
23 |
አረደውም፤ ሙሴን ከደሙ ወስዶ የአሮንን የቀኝ ጆሮውን ጫፍ፥ የቀኝ እጁንም አውራ ጣት የቀኝ እግሩንም አውራ ጣት አስነካው። |
24 |
የአሮንንም ልጆች አቀረበ፤ ሙሴም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀን እጃቸውንም አውራ ጣት፥ የቀኝ እግራቸውንም አውራ ጣት ከደሙ አስነካ፤ ሙሴም ደሙን በመሠዊያው ዙሪያ ረጨ። |
25 |
ስቡንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃውም ላይ ያለውን ስብ ሁሉ፥ የጕበቱንም መረብ፥ ሁለቱንም ኵላሊቶች ስባቸውንም፥ ቀኝ ወርቹንም ወሰደ፤ |
26 |
በእግዚአብሔር ፊት ካለው ከቂጣው እንጀራ ሌማት አንድ የቂጣ እንጐቻ፥ አንድም የዘይት እንጀራ፥ አንድም ስስ ቂጣ ወስዶ በስቡና በቀኝ ወርቹ ላይ አኖራቸው። |
27 |
ሁሉንም በአሮንና በልጆቹ እጆች ላይ አደረገ፥ በእግዚአብሔርም ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ወዘወዛቸው። |
28 |
ሙሴም ከእጃቸው ተቀብሎ በመሠዊያው በሚቃጠለው መሥዋዕት ላይ አቃጠለው፤ የጣፋጭ ሽታ መቀደሻ ነበረ። እርሱም ለእግዚአብሔር የእሳት ቁርባን ነበረ። |
29 |
ሙሴም ፍርምባውን ወስዶ በእግዚአብሔር ፊት ለመወዝወዝ ቍርባን ወዘወዘው፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘው ይህ ለቅድስና ከታረደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ። |
30 |
ሙሴም ከቅብዓቱ ዘይትና በመሠዊያው ላይ ካለው ከደሙ ወስዶ በአሮንና በልብሱ ላይ፥ በልጆቹና በልጆቹ ልብስ ላይ ረጨው፤ አሮንንና ልብሱንም፥ ልጆቹንም የልጆቹንም ልብስ ቀደሰ። |
31 |
ሙሴም አሮንንና ልጆቹን አላቸው። ሥጋውን በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ቀቅሉ፤ አሮንና ልጆቹ ይበሉታል ብዬ እንዳዘዝሁ በዚያ እርሱንና በሌማቱ ያለውን የቅድስናውን እንጀራ ብሉ። |
32 |
ከሥጋውና ከእንጀራውም የተረፈውን በእሳት ታቃጥሉታላችሁ። |
33 |
ሰባት ቀን ይክናችኋልና የክህነታችሁ ቀን እስኪፈጸም ድረስ ሰባት ቀን ከማኅበሩ ድንኳን ደጃፍ አትውጡ። |
34 |
በዚህ ቀን እንደ ተደረገ ለእናንተ ለማስተስረያ ይደረግ ዘንድ እንዲሁ እግዚአብሔር አዘዘ። |
35 |
እግዚአብሔር እንዲሁ አዝዞኛልና እንዳትሞቱ በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ሌሊቱንና ቀኑን ሰባት ቀን ተቀመጡ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓት ጠብቁ። |
36 |
አሮንና ልጆቹም እግዚአብሔር በሙሴ እጅ ያዘዘውን ሁሉ አደረጉ።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ዘሌዋውያን 8:1 |
ዘሌዋውያን 8:2 |
ዘሌዋውያን 8:3 |
ዘሌዋውያን 8:4 |
ዘሌዋውያን 8:5 |
ዘሌዋውያን 8:6 |
ዘሌዋውያን 8:7 |
ዘሌዋውያን 8:8 |
ዘሌዋውያን 8:9 |
ዘሌዋውያን 8:10 |
ዘሌዋውያን 8:11 |
ዘሌዋውያን 8:12 |
ዘሌዋውያን 8:13 |
ዘሌዋውያን 8:14 |
ዘሌዋውያን 8:15 |
ዘሌዋውያን 8:16 |
ዘሌዋውያን 8:17 |
ዘሌዋውያን 8:18 |
ዘሌዋውያን 8:19 |
ዘሌዋውያን 8:20 |
ዘሌዋውያን 8:21 |
ዘሌዋውያን 8:22 |
ዘሌዋውያን 8:23 |
ዘሌዋውያን 8:24 |
ዘሌዋውያን 8:25 |
ዘሌዋውያን 8:26 |
ዘሌዋውያን 8:27 |
ዘሌዋውያን 8:28 |
ዘሌዋውያን 8:29 |
ዘሌዋውያን 8:30 |
ዘሌዋውያን 8:31 |
ዘሌዋውያን 8:32 |
ዘሌዋውያን 8:33 |
ዘሌዋውያን 8:34 |
ዘሌዋውያን 8:35 |
ዘሌዋውያን 8:36 |
|
|
|
|
|
|
ዘሌዋውያን 1 / ዘሌዋ 1 |
ዘሌዋውያን 2 / ዘሌዋ 2 |
ዘሌዋውያን 3 / ዘሌዋ 3 |
ዘሌዋውያን 4 / ዘሌዋ 4 |
ዘሌዋውያን 5 / ዘሌዋ 5 |
ዘሌዋውያን 6 / ዘሌዋ 6 |
ዘሌዋውያን 7 / ዘሌዋ 7 |
ዘሌዋውያን 8 / ዘሌዋ 8 |
ዘሌዋውያን 9 / ዘሌዋ 9 |
ዘሌዋውያን 10 / ዘሌዋ 10 |
ዘሌዋውያን 11 / ዘሌዋ 11 |
ዘሌዋውያን 12 / ዘሌዋ 12 |
ዘሌዋውያን 13 / ዘሌዋ 13 |
ዘሌዋውያን 14 / ዘሌዋ 14 |
ዘሌዋውያን 15 / ዘሌዋ 15 |
ዘሌዋውያን 16 / ዘሌዋ 16 |
ዘሌዋውያን 17 / ዘሌዋ 17 |
ዘሌዋውያን 18 / ዘሌዋ 18 |
ዘሌዋውያን 19 / ዘሌዋ 19 |
ዘሌዋውያን 20 / ዘሌዋ 20 |
ዘሌዋውያን 21 / ዘሌዋ 21 |
ዘሌዋውያን 22 / ዘሌዋ 22 |
ዘሌዋውያን 23 / ዘሌዋ 23 |
ዘሌዋውያን 24 / ዘሌዋ 24 |
ዘሌዋውያን 25 / ዘሌዋ 25 |
ዘሌዋውያን 26 / ዘሌዋ 26 |
ዘሌዋውያን 27 / ዘሌዋ 27 |