1 |
እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው። |
2 |
ደግሞ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ በላቸው። ከእስራኤል ልጆች ወይም በእስራኤል ዘንድ ከሚቀመጡ እንግዶች ማናቸውም ሰው ዘሩን ለሞሎክ ቢሰጥ ፈጽሞ ይገደል፤ የአገሩ ሕዝብ በድንጋይ ይውገረው። |
3 |
መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የተቀደሰውንም ስሜን ያጐሰቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። |
4 |
ዘሩንም ለሞሎክ ሲሰጥ፥ የአገሩ ሕዝብ ያን ቸል ቢለው ባይገድሉትም፥ |
5 |
እኔ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ እርሱንም፥ ከሞሎክም ጋር ያመነዝሩ ዘንድ የሚከተሉትን ሁሉ ከሕዝባቸው መካከል ለይቼ አጠፋለሁ። |
6 |
መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም በሚከተል፥ በሥራቸውም በሚያመነዝር፥ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፥ ከሕዝቡም መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ። |
7 |
እንግዲህ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ። |
8 |
ሥርዓቴን ጠብቁ፥ አድርጉትም፤ እኔ የምቀድሳችሁ እግዚአብሔር ነኝ። |
9 |
ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፥ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፤ ደሙ በራሱ ላይ ነው። |
10 |
ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው ይገደሉ። |
11 |
ማናቸውም ሰው ከአባቱ ሚስት ጋር ቢተኛ የአባቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። |
12 |
ማናቸውም ሰው ከምራቱ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ፈጽመው ይገደሉ፤ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ደማቸውም በላያቸው ነው። |
13 |
ማናቸውም ሰው ከሴት ጋር እንደሚተኛ ከወንድ ጋር ቢተኛ ሁለቱ ጸያፍ ነገር አድርገዋል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። |
14 |
ማናቸውም ሰው እናቲቱንና ልጂቱን ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ በመካከላችሁ ኃጢአት እንዳይሆን እርሱና እነርሱ በእሳት ይቃጠሉ። |
15 |
ማናቸውም ሰው ከእንስሳ ጋር ቢገናኝ ፈጽሞ ይገደል፤ እንስሳይቱንም ግደሉአት። |
16 |
ማናቸይቱም ሴት ወደ እንስሳ ብትቀርብ፥ ከእርሱም ጋር ብትገናኝ፥ ሴቲቱንና እንስሳውን ግደል፤ ፈጽመው ይገደሉ፤ ደማቸው በላያቸው ነው። |
17 |
ማናቸውም ሰው የአባቱን ልጅ ወይም የእናቱን ልጅ እኅቱን ቢያገባ፥ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢያይ፥ እርስዋም ኃፍረተ ሥጋውን ብታይ፥ ይህ ጸያፍ ነገር ነው፤ በሕዝባቸውም ልጆች ፊት ይገደሉ፤ የእኅቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአልና ኃጢአቱን ይሸከማል። |
18 |
ማናቸውም ሰው ከባለ መርገም ሴት ጋር ቢተኛ ኃፍረተ ሥጋዋንም ቢገልጥ፥ ፈሳሽዋን ገልጦአልና፥ እርስዋም የደምዋን ፈሳሽ ገልጣለችና ሁለቱ ከሕዝባቸው መካከል ተለይተው ይጥፉ። |
19 |
የአባትህን ወይም የእናትህን እኅት ኃፍረተ ሥጋ አትግለጥ፤ ይህን የሚያደርግ የዘመድን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ። |
20 |
ሰውም ከአጎቱ ሚስት ጋር ቢተኛ፥ የአጎቱን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ኃጢአታቸውን ይሸከማሉ፤ ያለ ልጅ ይሞታሉ። |
21 |
ሰውም የወንድሙን ሚስት ቢያገባ ርኵሰት ነው፤ የወንድሙን ኃፍረተ ሥጋ ገልጦአል፤ ያለ ልጅ ይሆናሉ። |
22 |
እንግዲህ ትቀመጡባት ዘንድ የማገባችሁ ምድር እንዳትተፋችሁ ሥርዓቴን ሁሉ፥ ፍርዴንም ሁሉ ጠብቁ፥ አድርጉትም። |
23 |
ከፊታችሁ በምጥላቸውም ሕዝብ ወግ አትሂዱ፤ ይህን ሁሉ አድርገዋልና ተጸየፍኋቸው። |
24 |
ነገር ግን እናንተን። ምድራቸውን ትወርሳላችሁ፤ ትወርሱአትም ዘንድ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር እሰጣችኋለሁ አልኋችሁ። እኔ ከአሕዛብ የለየኋችሁ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነኝ። |
25 |
እንግዲህ ንጹሑን እንስሳ ከርኩሱ፥ ንጹሑንም ወፍ ከርኩስ ትለያላችሁ፤ ርኩሶች ናቸው ብዬ በለየኋቸው በእንስሳና በወፍ በምድርም ተንቀሳቃሽ ሁሉ ነፍሳችሁን አታርክሱ። |
26 |
እኔ እግዚአብሔር ቅዱስ ነኝና፥ ለእኔም ትሆኑ ዘንድ ከአሕዛብ ለይቻችኋለሁና ቅዱሳን ትሆኑልኛላችሁ። |
27 |
ሰው ወይም ሴት መናፍስትን ቢጠሩ ወይም ጠንቋዮች ቢሆኑ ፈጽመው ይገደሉ፤ በድንጋይ ይውገሩአቸው፤ ደማቸው በላያቸው ነው።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ዘሌዋውያን 20:1 |
ዘሌዋውያን 20:2 |
ዘሌዋውያን 20:3 |
ዘሌዋውያን 20:4 |
ዘሌዋውያን 20:5 |
ዘሌዋውያን 20:6 |
ዘሌዋውያን 20:7 |
ዘሌዋውያን 20:8 |
ዘሌዋውያን 20:9 |
ዘሌዋውያን 20:10 |
ዘሌዋውያን 20:11 |
ዘሌዋውያን 20:12 |
ዘሌዋውያን 20:13 |
ዘሌዋውያን 20:14 |
ዘሌዋውያን 20:15 |
ዘሌዋውያን 20:16 |
ዘሌዋውያን 20:17 |
ዘሌዋውያን 20:18 |
ዘሌዋውያን 20:19 |
ዘሌዋውያን 20:20 |
ዘሌዋውያን 20:21 |
ዘሌዋውያን 20:22 |
ዘሌዋውያን 20:23 |
ዘሌዋውያን 20:24 |
ዘሌዋውያን 20:25 |
ዘሌዋውያን 20:26 |
ዘሌዋውያን 20:27 |
|
|
|
|
|
|
ዘሌዋውያን 1 / ዘሌዋ 1 |
ዘሌዋውያን 2 / ዘሌዋ 2 |
ዘሌዋውያን 3 / ዘሌዋ 3 |
ዘሌዋውያን 4 / ዘሌዋ 4 |
ዘሌዋውያን 5 / ዘሌዋ 5 |
ዘሌዋውያን 6 / ዘሌዋ 6 |
ዘሌዋውያን 7 / ዘሌዋ 7 |
ዘሌዋውያን 8 / ዘሌዋ 8 |
ዘሌዋውያን 9 / ዘሌዋ 9 |
ዘሌዋውያን 10 / ዘሌዋ 10 |
ዘሌዋውያን 11 / ዘሌዋ 11 |
ዘሌዋውያን 12 / ዘሌዋ 12 |
ዘሌዋውያን 13 / ዘሌዋ 13 |
ዘሌዋውያን 14 / ዘሌዋ 14 |
ዘሌዋውያን 15 / ዘሌዋ 15 |
ዘሌዋውያን 16 / ዘሌዋ 16 |
ዘሌዋውያን 17 / ዘሌዋ 17 |
ዘሌዋውያን 18 / ዘሌዋ 18 |
ዘሌዋውያን 19 / ዘሌዋ 19 |
ዘሌዋውያን 20 / ዘሌዋ 20 |
ዘሌዋውያን 21 / ዘሌዋ 21 |
ዘሌዋውያን 22 / ዘሌዋ 22 |
ዘሌዋውያን 23 / ዘሌዋ 23 |
ዘሌዋውያን 24 / ዘሌዋ 24 |
ዘሌዋውያን 25 / ዘሌዋ 25 |
ዘሌዋውያን 26 / ዘሌዋ 26 |
ዘሌዋውያን 27 / ዘሌዋ 27 |