1 |
ለኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል፥ በወይን ጠጅ ለተሸነፉ በወፍራም ሸለቆአቸው ራስ ላይ ላለችም ለረገፈች ለክብሩ ጌጥ አበባ ወዮ! |
2 |
እነሆ፥ በጌታ ዘንድ ኃያል ብርቱ የሆነ አለ። እንደ በረዶ ወጨፎ፥ እንደሚያጠፋም ዐውሎ ነፋስ፥ እንደሚያጥለቀልቅም እንደ ታላቅ ውኃ ፈሳሽ በጠነከረ እጅ ወደ ምድር ይጥላል። |
3 |
የኤፍሬም ሰካሮች ትዕቢት አክሊል በእግር ይረገጣል፤ |
4 |
በወፍራሙ ሸለቆ ራስ ላይ ያለች የረገፈች የክብሩ ጌጥ አበባ ከመከር በፊት አስቀድማ እንደምትበስል በለስ ትሆናለች፤ ሰው ባያት ጊዜ በእጁ እንዳለች ይበላታል። |
5 |
በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤ |
6 |
በፍርድ ወንበር ላይ ለሚቀመጥም የፍርድ መንፈስ፥ ሰልፉን ወደ በር ለሚመልሱም ኃይል ይሆናል። |
7 |
እነዚህም ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይዋጣሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይፋንናሉ፤ በራእይ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ። |
8 |
ማዕዱ ሁሉ ትፋትንና ርኵሰትን ተሞልቶአታል፤ ንጹሕ ስፍራ እንኳ የለም። |
9 |
እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተዉ ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? |
10 |
ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ነው። |
11 |
በባዕድ አፍ በልዩም ልሳን ለዚህ ሕዝብ ይናገራል፤ እርሱም። ዕረፍት ይህች ናት፥ |
12 |
የደከመውን አሳርፉ፤ ይህችም ማረፊያ ናት አላቸው፤ እነርሱ ግን መስማትን እንቢ አሉ። |
13 |
ስለዚህ ሄደው ወደ ኋላ እንዲወድቁ እንዲሰበሩም ተጠምደውም እንዲያዙ የእግዚአብሔር ቃል ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ትእዛዝ በትእዛዝ፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ሥርዓት በሥርዓት፥ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ ይሆንላቸዋል። |
14 |
ስለዚህ በኢየሩሳሌም ያለውን ሕዝብ የምትገዙ ፌዘኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። |
15 |
እናንተም። ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም ስላላችሁ፥ |
16 |
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። እነሆ፥ በጽዮን ድንጋይን ለመሠረት አስቀምጣለሁ፤ የተፈተነውን፥ የከበረውን፥ መሠረቱ የጸናውን የማዕዘን ድንጋይ፤ የሚያምን አያፍርም። |
17 |
ለገመድ ፍርድን ለቱንቢም ጽድቅን አደርጋለሁ፤ በረዶውም የሐሰትን መሸሸጊያ ይጠርጋል፥ ውኆችም መሰወሪያውን ያሰጥማሉ። |
18 |
ከሞትም ጋር ያደረጋችሁት ቃል ኪዳን ይፈርሳል፥ ከሲኦልም ጋር የተማማላችሁት መሐላ አይጸናም፤ የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ ትረገጡበታላችሁ። |
19 |
ባለፈም ጊዜ ይወስዳችኋል፤ ማለዳ ማለዳ ቀንና ሌሊት ያልፋል፤ ወሬውንም ማስተዋል ድንጋጤ ይሆናል። |
20 |
ሰው በእርሱ ላይ ተዘርግቶ ቢተኛ አልጋው አጭር ነው፤ ሰውም ሰውነቱን መሸፈን ቢወድድ መጐናጸፊያ ጠባብ ነው። |
21 |
እግዚአብሔርም ሥራውን ማለት እንግዳ ሥራውን ይሠራ ዘንድ፥ አድራጎቱንም ማለት ያልታወቀውን አድራጎቱን ያደርግ ዘንድ በፐራሲም ተራራ እንደ ነበረ ይነሣል፥ በገባዖንም ሸለቆ እንደ ነበረ ይቈጣል። |
22 |
አሁንም በምድር ሁሉ ላይ የሚጸናውን የጥፋት ትእዛዝ ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ዘንድ ሰምቻለሁና እስራት እንዳይጸንባችሁ አታፊዙ። |
23 |
አድምጡ ድምፄንም ስሙ፤ ልብ አድርጉ ንግግሬንም ስሙ። |
24 |
በውኑ ገበሬ ሊዘራ ሁልጊዜ ያርሳልን? ወይስ ሁልጊዜ እርሻውን ይገለግላልን? |
25 |
ጓሉንስ ይከሰክሳልን? እርሻውን ባስተካከለ ጊዜ ጥቁሩን አዝሙድ፥ ከሙኑንም፥ ስንዴውንም በተርታ፥ ገብሱንም በስፍራው፥ አጃንም በደረጃው የሚዘራ አይደለምን? |
26 |
ይህንም ብልሃት አምላኩ ያስታውቀዋል ያስተምረውማል። |
27 |
ጥቁሩ አዝሙድ በተሳለች መሄጃ አያኬድም፥ የሰረገላም መንኰራኵር በከሙን ላይ አይዞርም፤ ነገር ግን ጥቁሩ አዝሙድ በሽመል ከሙኑም በበትር ይወቃል። |
28 |
የእንጀራ እህል ይደቅቃልን? ለዘላለም አያኬደውም፤ የሰረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቅቀውም። |
29 |
ይህም ደግሞ ድንቅ ምክር ከሚመክር በግብሩም ማለፊያ ከሆነው ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ወጥቶአል።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ኢሳይያስ 28:1 |
ኢሳይያስ 28:2 |
ኢሳይያስ 28:3 |
ኢሳይያስ 28:4 |
ኢሳይያስ 28:5 |
ኢሳይያስ 28:6 |
ኢሳይያስ 28:7 |
ኢሳይያስ 28:8 |
ኢሳይያስ 28:9 |
ኢሳይያስ 28:10 |
ኢሳይያስ 28:11 |
ኢሳይያስ 28:12 |
ኢሳይያስ 28:13 |
ኢሳይያስ 28:14 |
ኢሳይያስ 28:15 |
ኢሳይያስ 28:16 |
ኢሳይያስ 28:17 |
ኢሳይያስ 28:18 |
ኢሳይያስ 28:19 |
ኢሳይያስ 28:20 |
ኢሳይያስ 28:21 |
ኢሳይያስ 28:22 |
ኢሳይያስ 28:23 |
ኢሳይያስ 28:24 |
ኢሳይያስ 28:25 |
ኢሳይያስ 28:26 |
ኢሳይያስ 28:27 |
ኢሳይያስ 28:28 |
ኢሳይያስ 28:29 |
|
|
|
|
|
|
ኢሳይያስ 1 / ኢሳይያ 1 |
ኢሳይያስ 2 / ኢሳይያ 2 |
ኢሳይያስ 3 / ኢሳይያ 3 |
ኢሳይያስ 4 / ኢሳይያ 4 |
ኢሳይያስ 5 / ኢሳይያ 5 |
ኢሳይያስ 6 / ኢሳይያ 6 |
ኢሳይያስ 7 / ኢሳይያ 7 |
ኢሳይያስ 8 / ኢሳይያ 8 |
ኢሳይያስ 9 / ኢሳይያ 9 |
ኢሳይያስ 10 / ኢሳይያ 10 |
ኢሳይያስ 11 / ኢሳይያ 11 |
ኢሳይያስ 12 / ኢሳይያ 12 |
ኢሳይያስ 13 / ኢሳይያ 13 |
ኢሳይያስ 14 / ኢሳይያ 14 |
ኢሳይያስ 15 / ኢሳይያ 15 |
ኢሳይያስ 16 / ኢሳይያ 16 |
ኢሳይያስ 17 / ኢሳይያ 17 |
ኢሳይያስ 18 / ኢሳይያ 18 |
ኢሳይያስ 19 / ኢሳይያ 19 |
ኢሳይያስ 20 / ኢሳይያ 20 |
ኢሳይያስ 21 / ኢሳይያ 21 |
ኢሳይያስ 22 / ኢሳይያ 22 |
ኢሳይያስ 23 / ኢሳይያ 23 |
ኢሳይያስ 24 / ኢሳይያ 24 |
ኢሳይያስ 25 / ኢሳይያ 25 |
ኢሳይያስ 26 / ኢሳይያ 26 |
ኢሳይያስ 27 / ኢሳይያ 27 |
ኢሳይያስ 28 / ኢሳይያ 28 |
ኢሳይያስ 29 / ኢሳይያ 29 |
ኢሳይያስ 30 / ኢሳይያ 30 |
ኢሳይያስ 31 / ኢሳይያ 31 |
ኢሳይያስ 32 / ኢሳይያ 32 |
ኢሳይያስ 33 / ኢሳይያ 33 |
ኢሳይያስ 34 / ኢሳይያ 34 |
ኢሳይያስ 35 / ኢሳይያ 35 |
ኢሳይያስ 36 / ኢሳይያ 36 |
ኢሳይያስ 37 / ኢሳይያ 37 |
ኢሳይያስ 38 / ኢሳይያ 38 |
ኢሳይያስ 39 / ኢሳይያ 39 |
ኢሳይያስ 40 / ኢሳይያ 40 |
ኢሳይያስ 41 / ኢሳይያ 41 |
ኢሳይያስ 42 / ኢሳይያ 42 |
ኢሳይያስ 43 / ኢሳይያ 43 |
ኢሳይያስ 44 / ኢሳይያ 44 |
ኢሳይያስ 45 / ኢሳይያ 45 |
ኢሳይያስ 46 / ኢሳይያ 46 |
ኢሳይያስ 47 / ኢሳይያ 47 |
ኢሳይያስ 48 / ኢሳይያ 48 |
ኢሳይያስ 49 / ኢሳይያ 49 |
ኢሳይያስ 50 / ኢሳይያ 50 |
ኢሳይያስ 51 / ኢሳይያ 51 |
ኢሳይያስ 52 / ኢሳይያ 52 |
ኢሳይያስ 53 / ኢሳይያ 53 |
ኢሳይያስ 54 / ኢሳይያ 54 |
ኢሳይያስ 55 / ኢሳይያ 55 |
ኢሳይያስ 56 / ኢሳይያ 56 |
ኢሳይያስ 57 / ኢሳይያ 57 |
ኢሳይያስ 58 / ኢሳይያ 58 |
ኢሳይያስ 59 / ኢሳይያ 59 |
ኢሳይያስ 60 / ኢሳይያ 60 |
ኢሳይያስ 61 / ኢሳይያ 61 |
ኢሳይያስ 62 / ኢሳይያ 62 |
ኢሳይያስ 63 / ኢሳይያ 63 |
ኢሳይያስ 64 / ኢሳይያ 64 |
ኢሳይያስ 65 / ኢሳይያ 65 |
ኢሳይያስ 66 / ኢሳይያ 66 |