1 |
ስለ ጢሮስ የተነገረ ሸክም። የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ አልቅሱ፤ ፈርሶአልና ቤት የለም፥ መግባትም የለም፤ ከኪቲም አገር ጀምሮ ተገልጦላቸዋል። |
2 |
እናንተ በደሴት የምትኖሩ በባሕርም የምትሻገሩ የሲዶና ነጋዴዎች ንግድ የሞሉባችሁ ሆይ፥ ጸጥ በሉ። |
3 |
የሺሖር ዘርና የዓባይ ወንዝ መከር በብዙ ውኆች ላይ ገቢዋ ነበረ፤ እርስዋም የአሕዛብ መናገጃ ነበረች። |
4 |
ሲዶና ሆይ፥ ባሕር፥ የባሕር ምሽግ። አላማጥሁም፥ አልወለድሁም፤ ጐበዛዝትንም አላሳደግሁም፥ ደናግልንም አላሳደግሁም ብሎ ተናግሮአልና እፈሪ። |
5 |
ወሬዋ ወደ ግብጽ በደረሰ ጊዜ በጢሮስ ወሬ ምጥ ይይዛቸዋል። |
6 |
ወደ ተርሴስ ተሻገሩ፤ እናንተ በደሴት የምትኖሩ አልቅሱ። |
7 |
በቀድሞ ዘመን ተመሥርታ የነበረችው፥ በዚያም እንደ እንግዳ ሆና ትኖር ዘንድ እግሮችዋ ወደ ሩቅ ያፈለሱአት የደስታችሁ ከተማ ይህች ናትን? |
8 |
አክሊል ባስጫነች ከተማ በጢሮስ ላይ ይህን የወሰነ ማን ነው? ነጋዴዎችዋ አለቆች ናቸው፥ በእርስዋም የሚሸጡና የሚለውጡ የምድር ክቡራን ናቸው። |
9 |
የክብርን ሁሉ ትዕቢት ይሽር ዘንድ የምድርንም ክቡራን ሁሉ ያስንቅ ዘንድ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ወስኖታል። |
10 |
የተርሴስ ልጅ ሆይ፥ የሚከለክልሽ የለምና እንደ ዓባይ ወንዝ በአገርሽ ላይ ጐርፈሽ እለፊ። |
11 |
በባሕር ላይ እጁን ዘረጋ መንግሥታትንም አናወጠ፤ ምሽጎችዋንም ያጠፉ ዘንድ እግዚአብሔር ስለ ከነዓን አገር አዘዘ። |
12 |
እርሱም። አንቺ የተበደልሽ የሲዶና ድንግል ልጅ ሆይ፥ ከእንግዲህ ወዲህ ደስ አይበልሽ፤ ተነሥተሽ ወደ ኪቲም ተሻገሪ፥ በዚያም ደግሞ አታርፊም አለ። |
13 |
እነሆ፥ የከለዳውያን አገር! ይህ ሕዝብ ሆኖ አይገኝም፤ አሦራውያን ለምድረ በዳ አራዊት ሰጥተውታል፤ ግንቦቻቸውን ሠሩ፥ አዳራሾችዋንም አፈረሱ፥ ባድማም አደረጓት። |
14 |
እናንተ የተርሴስ መርከቦች ሆይ፥ ምሽጋችሁ ፈርሶአልና ዋይ በሉ። |
15 |
በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፤ ጢሮስ እንደ አንድ ንጉሥ ዘመን ሰባ ዓመት ያህል የተረሳች ትሆናለች፤ ከሰባ ዓመት በኋላ ግን ለጢሮስ በጋለሞታ ዘፈን እንደሚሆን እንዲሁ ይሆናል። |
16 |
አንቺ የተረሳሽ ጋለሞታ ሆይ፥ መሰንቆ ያዢ በከተማ ላይም ዙሪ፤ መታሰቢያም ይሆንልሽ ዘንድ ዜማን አሳምሪ ዘፈንሽንም አብዢ። |
17 |
ከሰባ ዓመትም በኋላ እግዚአብሔር ጢሮስን ይጐበኛታል፥ ወደ ዋጋዋም ትምለሳለች፥ ደግሞም በምድር ፊት ላይ ከሆኑ ከዓለም መንግሥታት ሁሉ ጋር ትገለሙታለች። |
18 |
ንግድዋና ዋጋዋ ለእግዚአብሔር የተቀደሰ ይሆናል፤ ንግድዋም በልተው ይጠግቡ ዘንድ ማለፊያም ልብስ ይለብሱ ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ለሚኖሩ ይሆናል እንጂ በዕቃ ቤትና በግምጃ ቤት ውስጥ አይከተትም።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ኢሳይያስ 23:1 |
ኢሳይያስ 23:2 |
ኢሳይያስ 23:3 |
ኢሳይያስ 23:4 |
ኢሳይያስ 23:5 |
ኢሳይያስ 23:6 |
ኢሳይያስ 23:7 |
ኢሳይያስ 23:8 |
ኢሳይያስ 23:9 |
ኢሳይያስ 23:10 |
ኢሳይያስ 23:11 |
ኢሳይያስ 23:12 |
ኢሳይያስ 23:13 |
ኢሳይያስ 23:14 |
ኢሳይያስ 23:15 |
ኢሳይያስ 23:16 |
ኢሳይያስ 23:17 |
ኢሳይያስ 23:18 |
|
|
|
|
|
|
ኢሳይያስ 1 / ኢሳይያ 1 |
ኢሳይያስ 2 / ኢሳይያ 2 |
ኢሳይያስ 3 / ኢሳይያ 3 |
ኢሳይያስ 4 / ኢሳይያ 4 |
ኢሳይያስ 5 / ኢሳይያ 5 |
ኢሳይያስ 6 / ኢሳይያ 6 |
ኢሳይያስ 7 / ኢሳይያ 7 |
ኢሳይያስ 8 / ኢሳይያ 8 |
ኢሳይያስ 9 / ኢሳይያ 9 |
ኢሳይያስ 10 / ኢሳይያ 10 |
ኢሳይያስ 11 / ኢሳይያ 11 |
ኢሳይያስ 12 / ኢሳይያ 12 |
ኢሳይያስ 13 / ኢሳይያ 13 |
ኢሳይያስ 14 / ኢሳይያ 14 |
ኢሳይያስ 15 / ኢሳይያ 15 |
ኢሳይያስ 16 / ኢሳይያ 16 |
ኢሳይያስ 17 / ኢሳይያ 17 |
ኢሳይያስ 18 / ኢሳይያ 18 |
ኢሳይያስ 19 / ኢሳይያ 19 |
ኢሳይያስ 20 / ኢሳይያ 20 |
ኢሳይያስ 21 / ኢሳይያ 21 |
ኢሳይያስ 22 / ኢሳይያ 22 |
ኢሳይያስ 23 / ኢሳይያ 23 |
ኢሳይያስ 24 / ኢሳይያ 24 |
ኢሳይያስ 25 / ኢሳይያ 25 |
ኢሳይያስ 26 / ኢሳይያ 26 |
ኢሳይያስ 27 / ኢሳይያ 27 |
ኢሳይያስ 28 / ኢሳይያ 28 |
ኢሳይያስ 29 / ኢሳይያ 29 |
ኢሳይያስ 30 / ኢሳይያ 30 |
ኢሳይያስ 31 / ኢሳይያ 31 |
ኢሳይያስ 32 / ኢሳይያ 32 |
ኢሳይያስ 33 / ኢሳይያ 33 |
ኢሳይያስ 34 / ኢሳይያ 34 |
ኢሳይያስ 35 / ኢሳይያ 35 |
ኢሳይያስ 36 / ኢሳይያ 36 |
ኢሳይያስ 37 / ኢሳይያ 37 |
ኢሳይያስ 38 / ኢሳይያ 38 |
ኢሳይያስ 39 / ኢሳይያ 39 |
ኢሳይያስ 40 / ኢሳይያ 40 |
ኢሳይያስ 41 / ኢሳይያ 41 |
ኢሳይያስ 42 / ኢሳይያ 42 |
ኢሳይያስ 43 / ኢሳይያ 43 |
ኢሳይያስ 44 / ኢሳይያ 44 |
ኢሳይያስ 45 / ኢሳይያ 45 |
ኢሳይያስ 46 / ኢሳይያ 46 |
ኢሳይያስ 47 / ኢሳይያ 47 |
ኢሳይያስ 48 / ኢሳይያ 48 |
ኢሳይያስ 49 / ኢሳይያ 49 |
ኢሳይያስ 50 / ኢሳይያ 50 |
ኢሳይያስ 51 / ኢሳይያ 51 |
ኢሳይያስ 52 / ኢሳይያ 52 |
ኢሳይያስ 53 / ኢሳይያ 53 |
ኢሳይያስ 54 / ኢሳይያ 54 |
ኢሳይያስ 55 / ኢሳይያ 55 |
ኢሳይያስ 56 / ኢሳይያ 56 |
ኢሳይያስ 57 / ኢሳይያ 57 |
ኢሳይያስ 58 / ኢሳይያ 58 |
ኢሳይያስ 59 / ኢሳይያ 59 |
ኢሳይያስ 60 / ኢሳይያ 60 |
ኢሳይያስ 61 / ኢሳይያ 61 |
ኢሳይያስ 62 / ኢሳይያ 62 |
ኢሳይያስ 63 / ኢሳይያ 63 |
ኢሳይያስ 64 / ኢሳይያ 64 |
ኢሳይያስ 65 / ኢሳይያ 65 |
ኢሳይያስ 66 / ኢሳይያ 66 |