1 |
የምድያምም ካህን የሙሴ አማት ዮቶር እግዚአብሔር ለሙሴና ለሕዝቡ ለእስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እስራኤልን ከግብፅ እንዳወጣ ሰማ። |
2 |
በዚያን ጊዜ የሙሴ አማት ዮቶር መልሶአት የነበረውን የሙሴን ሚስት ሲፓራን ሁለቱንም ልጆቿን ወሰደ። |
3 |
ከእነርሱ የአንደኛው ስም ጌርሳም ነበረ፤ አባቱ። በሌላ አገር ስደተኛ ነበርሁ ብሎአልና፤ |
4 |
የሁለተኛውም ስም አልዓዛር ነበረ። የአባቴ አምላክ ረዳኝ፥ ከፈርዖንም ሰይፍ አዳነኝ ብሎአልና። |
5 |
የሙሴ አማት ዮቶርም ከልጆቹና ከሚስቱ ጋር በእግዚአብሔር ተራራ አጠገብ በምድረ በዳ ወደ ሰፈረ ወደ ሙሴ መጣ። |
6 |
ሙሴንም። እኔ አማትህ ዮቶር፥ ሚስትህም፥ ከእርስዋም ጋር ሁለቱ ልጆችዋ መጥተንልሃል አለው። |
7 |
ሙሴም አማቱን ሊገናኝ ወጣ፥ ሰገደም፥ ሳመውም፤ እርስ በርሳቸውም ደኅንነታቸውን ተጠያየቁ፥ ወደ ድንኳኑም ገቡ። |
8 |
ሙሴም እግዚአብሔር በፈርዖንና በግብፃውያን ላይ ስለ እስራኤል ያደረገውን ሁሉ፥ በመንገድም ያገኛቸውን ድካም ሁሉ፥ እግዚአብሔርም እንዳዳናቸው ለአማቱ ነገረው። |
9 |
ዮቶርም እግዚአብሔር ለእስራኤል ስላደረገው ቸርነት ሁሉ፥ ከግብፃውያንም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው። |
10 |
ዮቶርም። ከግብፃውያንና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብፃውያንም እጅ ሕዝቡን ያዳነ እግዚአብሔር ይባረክ። |
11 |
ትዕቢት ባደረጉባቸው ነገር እግዚአብሔር ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አሁን አወቅሁ አለ። |
12 |
የሙሴ አማት ዮቶርም የሚቃጠል መሥዋዕትንና ሌላ መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እንጀራ ሊበሉ አሮን የእስራኤልም ሽማግሌዎች ሁሉ መጡ። |
13 |
እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር። |
14 |
የሙሴም አማት በሕዝቡ ያደረገውን ሁሉ ባየ ጊዜ። ይህ በሕዝቡ የምታደርገው ምንድር ነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ በዙሪያህ ቆመው ሳሉ አንተ ብቻህን ስለ ምን ተቀምጠሃል? አለው። |
15 |
ሙሴም አማቱን። ሕዝቡ እግዚአብሔርን ለመጠየቅ ወደ እኔ ይመጣሉ፤ |
16 |
ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው። |
17 |
የሙሴም አማት አለው። አንተ የምታደርገው ይህ ነገር መልካም አይደለም። |
18 |
ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። |
19 |
አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤ |
20 |
ሥርዓቱንም ሕጉንም አስተምራቸው፥ የሚሄዱበትን መንገድ የሚያደርጉትንም ሥራ ሁሉ አሳያቸው። |
21 |
አንተም ከሕዝቡ ሁሉ አዋቂዎችን፥ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን፥ የታመኑ፥ የግፍንም ረብ የሚጠሉትን ሰዎች ምረጥ፤ ከእነርሱም የሺህ አለቆችን፥ የመቶ አለቆችን፥ የአምሳ አለቆችን፥ የአሥርም አለቆችን ሹምላቸው። |
22 |
በሕዝቡ ላይ ሁልጊዜ ይፍረዱ፤ አውራውን ነገር ሁሉ ወደ አንተ ያምጡት፥ ታናሹንም ነገር ሁሉ እነርሱ ይፍረዱ፤ እነርሱም ከአንተ ጋር ሸክሙን ይሸከማሉ፥ ለአንተም ይቀልልልሃል። |
23 |
ይህንም ብታደርግ፥ እግዚአብሔር እንዲሁ ቢያዝዝህ፥ መቆም ይቻልሃል፥ ደግሞም ይህ ሕዝብ ሁሉ በሰላም ወደ ስፍራው ይደርሳል። |
24 |
ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፥ ያለውንም ሁሉ አደረገ። |
25 |
ሙሴም ከእስራኤል ሁሉ አዋቂዎችን መረጠ፥ በሕዝቡም ላይ የሺህ አለቆች፥ የመቶም አለቆች፥ የአምሳም አለቆች፥ የአሥርም አለቆች አድርጎ ሾማቸው። |
26 |
በሕዝቡም ላይ ሁልጊዜ ፈረዱ፤ የከበደባቸውንም ነገር ወደ ሙሴ አመጡ፥ ታናሹን ነገር ሁሉ ግን እነርሱ ፈረዱ። |
27 |
ሙሴም አማቱን ሰደደው፤ እርሱም ወደ አገሩ ተመለሰ።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ዘፀአት 18:1 |
ዘፀአት 18:2 |
ዘፀአት 18:3 |
ዘፀአት 18:4 |
ዘፀአት 18:5 |
ዘፀአት 18:6 |
ዘፀአት 18:7 |
ዘፀአት 18:8 |
ዘፀአት 18:9 |
ዘፀአት 18:10 |
ዘፀአት 18:11 |
ዘፀአት 18:12 |
ዘፀአት 18:13 |
ዘፀአት 18:14 |
ዘፀአት 18:15 |
ዘፀአት 18:16 |
ዘፀአት 18:17 |
ዘፀአት 18:18 |
ዘፀአት 18:19 |
ዘፀአት 18:20 |
ዘፀአት 18:21 |
ዘፀአት 18:22 |
ዘፀአት 18:23 |
ዘፀአት 18:24 |
ዘፀአት 18:25 |
ዘፀአት 18:26 |
ዘፀአት 18:27 |
|
|
|
|
|
|
ዘፀአት 1 / ዘፀአት 1 |
ዘፀአት 2 / ዘፀአት 2 |
ዘፀአት 3 / ዘፀአት 3 |
ዘፀአት 4 / ዘፀአት 4 |
ዘፀአት 5 / ዘፀአት 5 |
ዘፀአት 6 / ዘፀአት 6 |
ዘፀአት 7 / ዘፀአት 7 |
ዘፀአት 8 / ዘፀአት 8 |
ዘፀአት 9 / ዘፀአት 9 |
ዘፀአት 10 / ዘፀአት 10 |
ዘፀአት 11 / ዘፀአት 11 |
ዘፀአት 12 / ዘፀአት 12 |
ዘፀአት 13 / ዘፀአት 13 |
ዘፀአት 14 / ዘፀአት 14 |
ዘፀአት 15 / ዘፀአት 15 |
ዘፀአት 16 / ዘፀአት 16 |
ዘፀአት 17 / ዘፀአት 17 |
ዘፀአት 18 / ዘፀአት 18 |
ዘፀአት 19 / ዘፀአት 19 |
ዘፀአት 20 / ዘፀአት 20 |
ዘፀአት 21 / ዘፀአት 21 |
ዘፀአት 22 / ዘፀአት 22 |
ዘፀአት 23 / ዘፀአት 23 |
ዘፀአት 24 / ዘፀአት 24 |
ዘፀአት 25 / ዘፀአት 25 |
ዘፀአት 26 / ዘፀአት 26 |
ዘፀአት 27 / ዘፀአት 27 |
ዘፀአት 28 / ዘፀአት 28 |
ዘፀአት 29 / ዘፀአት 29 |
ዘፀአት 30 / ዘፀአት 30 |
ዘፀአት 31 / ዘፀአት 31 |
ዘፀአት 32 / ዘፀአት 32 |
ዘፀአት 33 / ዘፀአት 33 |
ዘፀአት 34 / ዘፀአት 34 |
ዘፀአት 35 / ዘፀአት 35 |
ዘፀአት 36 / ዘፀአት 36 |
ዘፀአት 37 / ዘፀአት 37 |
ዘፀአት 38 / ዘፀአት 38 |
ዘፀአት 39 / ዘፀአት 39 |
ዘፀአት 40 / ዘፀአት 40 |