1 |
አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት። |
2 |
የባሪያዎችህንም በድኖች ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፥ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤ |
3 |
ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ። |
4 |
ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት። |
5 |
አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል? |
6 |
ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ፤ |
7 |
ያዕቆብን በልተውታልና፥ ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና። |
8 |
የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና። |
9 |
አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን። |
10 |
አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤ |
11 |
የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን። |
12 |
አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው። |
13 |
እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘላለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |