1 |
በእውነት ጽድቅን ብትናገሩስ፥ የሰው ልጆች ሆይ፥ በቅን ትፈርዳላችሁ፤ |
2 |
በልባችሁ በምድር ላይ ኃጢአትን ትሠራላችሁና፥ እጆቻችሁም ግፍን ይታታሉና። |
3 |
ኅጥኣን ከማኅፀን ጀምረው ተለዩ፤ ከሆድም ጀምረው ሳቱ፥ ሐሰትንም ተናገሩ። |
4 |
ቍጣቸው እንደ እባብ መርዝ ነው፥ እንደ ምድር አውሬም ጆሮዋ የተደፈነ ነው፥ |
5 |
አዋቂ ሲደግምባት የአስማተኛውን ቃል እንደማትሰማ። |
6 |
እግዚአብሔር ጥርሳቸውን በአፋቸው ውስጥ ይሰብራል፤ እግዚአብሔር የአንበሶቹን መንጋጋቸውን ያደቅቃል። |
7 |
እንደሚፈስስ ውኃ ይቀልጣሉ፤ እስኪያደክማቸው ድረስ ፍላጾቹን ይገትራል። |
8 |
እንደሚቀልጥ ሰም ያልቃሉ፤ እሳት ወደቀች፥ ፀሐይንም አላዩአትም። |
9 |
እሾኻችሁ ሳይታወቅ በትር ሆነ፤ ሕያዋን ሳላችሁ በመዓቱ ይነጥቃችኋል። |
10 |
ጻድቅ በቀልን ባየ ጊዜ ደስ ይለዋል፤ በኃጢአተኛው ደምም እጁን ይታጠባል። |
11 |
ሰውም። በእውነት ለጻድቅ ፍሬ አለው፤ በእውነት በምድር ላይ የሚፈርድ አምላክ አለ ይላል።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |