1 |
ኢዮብም መለሰ እንዲህም አለ። |
2 |
በእውነት እንዲህ እንደ ሆነ አወቅሁ፤ ሰውስ በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ መሆን እንዴት ይችላል? |
3 |
ከእርሱ ጋር ይከራከር ዘንድ ቢወድድ፥ ከሺህ ነገር አንዱን መመለስ አይችልም። |
4 |
ልቡ ጠቢብ፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፤ ደፍሮትስ በደኅና የሄደ ማን ነው? |
5 |
ተራሮችን ይነቅላል፤ አያውቁትም፤ በቍጣውም ይገለብጣቸዋል። |
6 |
ምድርን ከስፍራው ያናውጣታል፥ ምሰሶችዋም ይንቀጠቀጣሉ። |
7 |
ፀሐይን ያዝዛታል፥ አትወጣምም፤ ከዋክብትንም ያትማል። |
8 |
ሰማያትን ብቻውን ይዘረጋል፥ በባሕሩም ማዕበል ላይ ይረግጣል። |
9 |
ድብ የሚባለውን ኮከብና ኦሪዮን የሚባለውን ኮከብ፥ ሰባቱንም ከዋክብት፥ በደቡብም በኩል ያሉትን የከዋክብት ማደርያዎች ሠርቶአል። |
10 |
የማይመረመረውን ታላላቅ ነገር፥ የማይቈጠረውንም ተአምራት ያደርጋል። |
11 |
እነሆ፥ ቢመጣብኝ አላየውም፤ ቢያልፍብኝም አላውቀውም። |
12 |
እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ። ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው? |
13 |
እግዚአብሔር ቍጣውን አይመልስም፤ ከእርሱ በታች ረዓብን የሚረዱ ይዋረዳሉ። |
14 |
ይልቁንስ እመልስለት ዘንድ፥ ቃሌንስ በፊቱ እመርጥ ዘንድ እኔ ማን ነኝ? |
15 |
ጻድቅ ብሆን ኖሮ አልመልስለትም ነበር፤ ወደ ፈራጄም እለምን ነበር። |
16 |
ብጠራው እርሱም ቢመልስልኝ ኖሮ፥ ቃሌን እንደ ሰማ አላምንም ነበር። |
17 |
በዐውሎ ነፋስ ይሰብረኛል፥ ቍስሌንም ያለ ምክንያት ያበዛል። |
18 |
እተነፍስ ዘንድ አይተወኝም፥ ነገር ግን መራራን ነገር አጥግቦኛል። |
19 |
የኃይል ነገር ቢሆን እርሱ ኃያል ነው፤ የፍርድ ነገር ቢሆን። ጊዜን ወሳኙ ማን ነው? ይላል። |
20 |
ጻድቅ ብሆን አፌ ይወቅሰኛል፤ ፍጹምም ብሆን ጠማማ ያደርገኛል። |
21 |
ፍጹም ነኝ ራሴንም አልመለከትም፤ ሕይወቴንም እንቃታለሁ። |
22 |
ይህ ሁሉ አንድ ነው፤ ስለዚህ። ፍጹማንንና ክፉዎችን ያጠፋል እላለሁ። |
23 |
መቅሠፍቱ ፈጥኖ ቢገድል፥ በንጹሐን ፈተና ይሳለቃል። |
24 |
ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፤ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፤ እርሱ ካልሆነ ማን ነው? |
25 |
ዘመኔ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናል፤ ይሸሻል፥ መልካምንም አያይም። |
26 |
የደንገል ታንኳ እንደሚፈጥን፥ ንስርም ወደ ንጥቂያው እንደሚበርር ያልፋል። |
27 |
እኔ። የኀዘን እንጕርጕሮዬን እረሳለሁ፤ ፊቴን መልሼ እጽናናለሁ ብል፥ |
28 |
ንጹሕ እንደማታደርገኝ እኔ አውቃለሁና ከመከራዬ ሁሉ እፈራለሁ። |
29 |
በደለኛ እንደሚሆን ሰው እሆናለሁ፤ ስለ ምንስ በከንቱ እደክማለሁ? |
30 |
በአመዳይ ውስጥ ብታጠብ፥ እጆቼንም እጅግ ባነጻ፥ |
31 |
በአዘቅት ውስጥ ታሰጥመኛለህ፥ ልብሴም ይጸየፈኛል። |
32 |
እንድመልስለት አብረን ወደ ፍርድ እንገባ ዘንድ፥ እርሱ እንደ እኔ ሰው አይደለም። |
33 |
እጁን በሁለታችን ላይ የሚያኖር ዳኛ በመካከላችን ምነው በተገኘ! |
34 |
በትሩን ከእኔ ላይ ያርቅ፥ ግርማውም አያስፈራኝ፤ |
35 |
እናገርም ነበር፥ አልፈራውምም ነበር፤ በራሴ እንዲህ አይደለሁምና።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ኢዮብ 9:1 |
ኢዮብ 9:2 |
ኢዮብ 9:3 |
ኢዮብ 9:4 |
ኢዮብ 9:5 |
ኢዮብ 9:6 |
ኢዮብ 9:7 |
ኢዮብ 9:8 |
ኢዮብ 9:9 |
ኢዮብ 9:10 |
ኢዮብ 9:11 |
ኢዮብ 9:12 |
ኢዮብ 9:13 |
ኢዮብ 9:14 |
ኢዮብ 9:15 |
ኢዮብ 9:16 |
ኢዮብ 9:17 |
ኢዮብ 9:18 |
ኢዮብ 9:19 |
ኢዮብ 9:20 |
ኢዮብ 9:21 |
ኢዮብ 9:22 |
ኢዮብ 9:23 |
ኢዮብ 9:24 |
ኢዮብ 9:25 |
ኢዮብ 9:26 |
ኢዮብ 9:27 |
ኢዮብ 9:28 |
ኢዮብ 9:29 |
ኢዮብ 9:30 |
ኢዮብ 9:31 |
ኢዮብ 9:32 |
ኢዮብ 9:33 |
ኢዮብ 9:34 |
ኢዮብ 9:35 |
|
|
|
|
|
|
ኢዮብ 1 / ኢዮብ 1 |
ኢዮብ 2 / ኢዮብ 2 |
ኢዮብ 3 / ኢዮብ 3 |
ኢዮብ 4 / ኢዮብ 4 |
ኢዮብ 5 / ኢዮብ 5 |
ኢዮብ 6 / ኢዮብ 6 |
ኢዮብ 7 / ኢዮብ 7 |
ኢዮብ 8 / ኢዮብ 8 |
ኢዮብ 9 / ኢዮብ 9 |
ኢዮብ 10 / ኢዮብ 10 |
ኢዮብ 11 / ኢዮብ 11 |
ኢዮብ 12 / ኢዮብ 12 |
ኢዮብ 13 / ኢዮብ 13 |
ኢዮብ 14 / ኢዮብ 14 |
ኢዮብ 15 / ኢዮብ 15 |
ኢዮብ 16 / ኢዮብ 16 |
ኢዮብ 17 / ኢዮብ 17 |
ኢዮብ 18 / ኢዮብ 18 |
ኢዮብ 19 / ኢዮብ 19 |
ኢዮብ 20 / ኢዮብ 20 |
ኢዮብ 21 / ኢዮብ 21 |
ኢዮብ 22 / ኢዮብ 22 |
ኢዮብ 23 / ኢዮብ 23 |
ኢዮብ 24 / ኢዮብ 24 |
ኢዮብ 25 / ኢዮብ 25 |
ኢዮብ 26 / ኢዮብ 26 |
ኢዮብ 27 / ኢዮብ 27 |
ኢዮብ 28 / ኢዮብ 28 |
ኢዮብ 29 / ኢዮብ 29 |
ኢዮብ 30 / ኢዮብ 30 |
ኢዮብ 31 / ኢዮብ 31 |
ኢዮብ 32 / ኢዮብ 32 |
ኢዮብ 33 / ኢዮብ 33 |
ኢዮብ 34 / ኢዮብ 34 |
ኢዮብ 35 / ኢዮብ 35 |
ኢዮብ 36 / ኢዮብ 36 |
ኢዮብ 37 / ኢዮብ 37 |
ኢዮብ 38 / ኢዮብ 38 |
ኢዮብ 39 / ኢዮብ 39 |
ኢዮብ 40 / ኢዮብ 40 |
ኢዮብ 41 / ኢዮብ 41 |
ኢዮብ 42 / ኢዮብ 42 |