1 |
ኢዮብም ምሳሌውን ይመስል ዘንድ ደገመ፥ እንዲህም አለ። |
2 |
ፍርዴን ያስወገደ ሕያው እግዚአብሔርን! ነፍሴንም መራራ ያደረገ ሁሉን የሚችል ሕያው አምላክን! |
3 |
እስትንፋሴ በእኔ ውስጥ፥ የእግዚአብሔርም መንፈስ በአፍንጫዬ ውስጥ ገና ሳለ፥ |
4 |
ከንፈሬ ኃጢአትን አትናገርም፥ አንደበቴም ሽንገላን አያወጣም። |
5 |
እናንተን ማጽደቅ ከእኔ ዘንድ ይራቅ፤ እስክሞት ድረስ ፍጹምነቴን ከእኔ አላርቅም። |
6 |
ጽድቄን እይዛለሁ እርሱንም አልተውም፤ ከቀኖቼም ሁሉ ስለ አንዱ ልቤ አይዘልፈኝም። |
7 |
ጠላቴ እንደ በደለኛ፥ በእኔ ላይም የሚነሣ እንደ ኃጢአተኛ ይሁን። |
8 |
እግዚአብሔር ባጠፋውና ነፍሱን በለየ ጊዜ፥ የዝንጉ ሰው ተስፋው ምንድር ነው? |
9 |
በውኑ መከራ በመጣበት ጊዜ፥ እግዚአብሔር ጩኸቱን ይሰማልን? |
10 |
ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን? |
11 |
እኔ ስለ እግዚአብሔር እጅ አስተምራችኋለሁ፤ ሁሉን በሚችል አምላክ ዘንድ ያለውን አልሸሽግም። |
12 |
እነሆ፥ ሁላችሁ አይታችኋል፤ ስለ ምን ከንቱ ሆናችሁ? |
13 |
ይህች ከእግዚአብሔር ዘንድ የበደለኛ እድል ፈንታ፥ ግፈኛም ሁሉን ከሚችል አምላክ ዘንድ የሚቀበላት ርስት ናት፤ |
14 |
ልጆቹ ቢበዙ ለሰይፍ ይሆናሉ፤ ዘሩም እንጀራን አይጠግብም። |
15 |
ለእርሱም የቀሩት በቸነፈር ይቀበራሉ፤ መበለቶቻቸውም አያለቅሱም። |
16 |
እርሱ ብርን እንደ አፈር ቢከምር፥ ልብስንም እንደ ጭቃ ቢያዘጋጅ፥ |
17 |
እርሱ ያዘጋጀው ይሆናል፥ ነገር ግን ጻድቅ ይለብሰዋል፤ ብሩንም ንጹሐን ይከፋፈሉታል። |
18 |
የሚሠራው ቤት እንደ ሸረሪት ድር ይሠራል፥ ጠባቂም እንደሚሠራው ጎጆ ነው። |
19 |
ባለጠጋ ሆኖ ይተኛል፥ ዳግመኛም አይተኛም፤ ዓይኑን ይከፍታል፥ እርሱም የለም። |
20 |
ድንጋጤ እንደ ጐርፍ ታገኘዋለች፤ በሌሊትም ዐውሎ ነፋስ ትነጥቀዋለች። |
21 |
የምሥራቅ ነፋስ ያነሣዋል፥ እርሱም ይሄዳል፤ ከቦታውም ይጠርገዋል። |
22 |
እርሱ ይጥልበታል፥ አይራራለትም፤ ከእጁ ፈጥኖ መሸሽ ይወድዳል። |
23 |
ሰው በእጁ ያጨበጭብበታል፤ ከስፍራውም በፉጨት ያስወጡታል።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ኢዮብ 27:1 |
ኢዮብ 27:2 |
ኢዮብ 27:3 |
ኢዮብ 27:4 |
ኢዮብ 27:5 |
ኢዮብ 27:6 |
ኢዮብ 27:7 |
ኢዮብ 27:8 |
ኢዮብ 27:9 |
ኢዮብ 27:10 |
ኢዮብ 27:11 |
ኢዮብ 27:12 |
ኢዮብ 27:13 |
ኢዮብ 27:14 |
ኢዮብ 27:15 |
ኢዮብ 27:16 |
ኢዮብ 27:17 |
ኢዮብ 27:18 |
ኢዮብ 27:19 |
ኢዮብ 27:20 |
ኢዮብ 27:21 |
ኢዮብ 27:22 |
ኢዮብ 27:23 |
|
|
|
|
|
|
ኢዮብ 1 / ኢዮብ 1 |
ኢዮብ 2 / ኢዮብ 2 |
ኢዮብ 3 / ኢዮብ 3 |
ኢዮብ 4 / ኢዮብ 4 |
ኢዮብ 5 / ኢዮብ 5 |
ኢዮብ 6 / ኢዮብ 6 |
ኢዮብ 7 / ኢዮብ 7 |
ኢዮብ 8 / ኢዮብ 8 |
ኢዮብ 9 / ኢዮብ 9 |
ኢዮብ 10 / ኢዮብ 10 |
ኢዮብ 11 / ኢዮብ 11 |
ኢዮብ 12 / ኢዮብ 12 |
ኢዮብ 13 / ኢዮብ 13 |
ኢዮብ 14 / ኢዮብ 14 |
ኢዮብ 15 / ኢዮብ 15 |
ኢዮብ 16 / ኢዮብ 16 |
ኢዮብ 17 / ኢዮብ 17 |
ኢዮብ 18 / ኢዮብ 18 |
ኢዮብ 19 / ኢዮብ 19 |
ኢዮብ 20 / ኢዮብ 20 |
ኢዮብ 21 / ኢዮብ 21 |
ኢዮብ 22 / ኢዮብ 22 |
ኢዮብ 23 / ኢዮብ 23 |
ኢዮብ 24 / ኢዮብ 24 |
ኢዮብ 25 / ኢዮብ 25 |
ኢዮብ 26 / ኢዮብ 26 |
ኢዮብ 27 / ኢዮብ 27 |
ኢዮብ 28 / ኢዮብ 28 |
ኢዮብ 29 / ኢዮብ 29 |
ኢዮብ 30 / ኢዮብ 30 |
ኢዮብ 31 / ኢዮብ 31 |
ኢዮብ 32 / ኢዮብ 32 |
ኢዮብ 33 / ኢዮብ 33 |
ኢዮብ 34 / ኢዮብ 34 |
ኢዮብ 35 / ኢዮብ 35 |
ኢዮብ 36 / ኢዮብ 36 |
ኢዮብ 37 / ኢዮብ 37 |
ኢዮብ 38 / ኢዮብ 38 |
ኢዮብ 39 / ኢዮብ 39 |
ኢዮብ 40 / ኢዮብ 40 |
ኢዮብ 41 / ኢዮብ 41 |
ኢዮብ 42 / ኢዮብ 42 |