A A A A A
Facebook Instagram Twitter
የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (Selassie) 1962

2 ዜና መዋዕል 321
ከዚህም ነገርና ከዚህ እምነት በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም መጥቶ ወደ ይሁዳ ገባ፥ በተመሸጉትም ከተሞች ፊት ሰፈረ፥ ሊወስዳቸውም አሰበ።
2
ሕዝቅያስም ሰናክሬም እንደ መጣ፥ ኢየሩሳሌምንም ሊወጋ ፊቱን አንዳቀና ባየ ጊዜ፥
3
ከከተማይቱ በስተ ውጭ ያለውን የውኃውን ምንጭ ይደፍኑ ዘንድ ከአለቆቹና ከኃያላኑ ጋር ተማከረ፤ እነርሱም ረዱት።
4
እጅግም ሰዎች ተሰብስበው። የአሦር ነገሥታት መጥተው ብዙ ውኃ ስለ ምን ያገኛሉ? ብለው ምንጩን ሁሉ፥ በምድርም መካከል ይንዶለዶል የነበረውን ወንዝ ደፈኑ።
5
ሰውነቱንም አጸናና፥ የፈረሰውንም ቅጥር ሁሉ ጠገነ፥ በላዩም ግንብ ሠራበት፥ ከእርሱም በስተ ውጭ ሌላ ቅጥር ሠራ፤ በዳዊትም ከተማ ያለችውን ሚሎን አጠነከረ፤ ብዙም መሣሪያና ጋሻ ሠራ።
6
የጦር አለቆቹንም በሕዝቡ ላይ ሾሞ፥ ሁሉንም በከተማይቱ በር ወዳለው አደባባይ ሰብስቦ።
7
ጽኑ፥ አይዞአችሁ፤ ከእኛም ጋር ያለው ከእርሱ ጋር ካለው ይበልጣልና ከአሦር ንጉሥና ከእርሱ ጋር ካለው ጭፍራ ሁሉ አትፍሩ፥ አትደንግጡም።
8
ከእርሱ ጋር የሥጋ ክንድ ነው፤ ከእኛ ጋር ያለው ግን የሚረዳንና የሚዋጋልን አምላካችን እግዚአብሔር ነው ብሎ አጸናናቸው። ሕዝቡም በይሁዳ ንጉሥ በሕዝቅያስ ቃል ተጽናና።
9
ከዚህም በኋላ የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም ከሠራዊቱ ሁሉ ጋር በለኪሶ ፊት ሳለ ባሪያዎቹን ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ይሁዳ ንጉሥ ወደ ሕዝቅያስና በኢየሩሳሌም ወደ ነበሩ ወደ ይሁዳ ሁሉ እንዲህ ሲል ላከ።
10
የአሦር ንጉሥ ሰናክሬም እንዲህ ይላል። እናንተ በማን ተማምናችሁ በኢየሩሳሌም ምሽግ ትቀመጣላችሁ?
11
አምላካችን እግዚአብሔር ከአሦር ንጉሥ እጅ ያድነናል እያለ በራብና በጥም እንድትሞቱ አሳልፎ ይሰጣችሁ ዘንድ የሚያባብላችሁ ሕዝቅያስ አይደለምን?
12
በአንድ መሠዊያ ፊት ስገዱ፥ በእርሱም ላይ ዕጠኑ እያለ ይሁዳንና ኢየሩሳሌምን አዝዞ፥ የኮረብታው መስገጃዎቹና መሠዊያዎቹን ያፈረሰ ይህ ሕዝቅያስ አይደለምን?
13
እኔና አባቶቼ በምድር አሕዛብ ሁሉ ያደረግነውን አላወቃችሁምን? የምድርስ ሁሉ አሕዛብ አማልክት አገራቸውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ በውኑ ተቻላቸውን?
14
አምላካችሁስ ከእጄ እናንተን ለማዳን ይችል ዘንድ አባቶቼ ካጠፉአቸው ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ የቻለ ማን ነው?
15
አሁንም ሕዝቅያስ አያስታችሁ፥ እንዲህም አያባብላችሁ፥ አትመኑትም፤ ከአሕዛብና ከመንግሥታት አማልክት ሁሉ ሕዝቡን ከእጄና ከአባቶቼ እጅ ያድን ዘንድ ዘንድ ማንም አልቻለም፤ ይልቁንስ አምላካችሁ ከእጄ ያድናችሁ ዘንድ እንዴት ይችላል?
16
ባሪያዎቹም ደግሞ በአምላክ በእግዚአብሔርና በባሪያው በሕዝቅያስ ላይ ሌላ ብዙ ነገር ተናገሩ።
17
ደግሞም የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለመስደብ፥ በእርሱም ላይ ለመናገር። የምድር አሕዛብ አማልክት ሕዝባቸውን ከእጄ ያድኑ ዘንድ እንዳልቻሉ፥ እንዲሁ የሕዝቅያስ አምላክ ሕዝቡን ከእጄ ያድን ዘንድ አይችልም የሚል ደብዳቤ ጻፈ።
18
ከተማይቱንም እንዲወስዱ፥ በቅጥር ላይ የተቀመጡትን የኢየሩሳሌም ሕዝብ ያስፈሩና ያስደነግጡ ዘንድ፥ በታላቅ ድምፅ በዕብራይስጥ ቋንቋ ይጮኹባቸው ነበር።
19
በሰውም እጅ በተሠሩ በምድር አሕዛብ አማልክት ላይ አንደሚናገሩ መጠን በኢየሩሳሌም አምላክ ላይ ተናገሩ።
20
ንጉሡም ሕዝቅያስና የአሞጽ ልጅ ነቢዩ ኢሳይያስ ስለዚህ ጸለዩ፥ ወደ ሰማይም ጮኹ።
21
እግዚአብሔርም ጽኑዓን ኃያላኑንና መሳፍንቱን አለቆቹንም ከአሦር ንጉሥ ሰፈር እንዲያጠፋ መልአኩን ሰደደ። የአሦርም ንጉሥ አፍሮ ወደ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩም ቤት በገባ ጊዜ ከወገቡ የወጡት ልጆቹ በዚያ በሰይፍ ገደሉት።
22
እንዲሁም እግዚአብሔር ሕዝቅያስንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ከአሦር ንጉሥ ከሰናክሬም እጅ ከሁሉም እጅ አዳናቸው፤ በዙሪያቸውም ካለው ሁሉ አሳረፋቸው።
23
ብዙዎቹም ለእግዚአብሔር መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፥ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።
24
በዚያም ወራት ሕዝቅያስ እስኪሞት ድረስ ታመመ፥ ወደ እግዚአብሔርም ጸለየ፤ እርሱም ተናገረው፥ ምልክትም ሰጠው።
25
ሕዝቅያስ ግን እንደ ተቀበለው ቸርነት መጠን አላደረገም፥ ልቡም ኰራ፤ ስለዚህም በእርሱና በይሁዳ በኢየሩሳሌምም ላይ ቍጣ ሆነ።
26
ሕዝቅያስም ከኢየሩሳሌም ሰዎች ጋር ስለ ልቡ ኵራት ሰውነቱን አዋረደ፥ የእግዚአብሔርም ቍጣ በሕዝቅያስ ዘመን አልመጣባቸውም።
27
ለሕዝቅያስም እጅግ ብዙ ሀብትና ክብር ነበረው፤ ለብርና ለወርቅም፥ ለከበረው ዕንቍና ለሽቱው፥ ለጋሻውና ለከበረው ዕቃ ሁሉ ግምጃ ቤቶች ሠራ።
28
ለእህልና ለወይን ጠጅም ለዘይትም ዕቃ ቤቶች፥ ለልዩ ልዩም እንስሳ ጋጥ፥ ለመንጎችም በረት ሠራ።
29
እግዚአብሔርም እጅግ ብዙ ጥሪት ሰጥቶት ነበርና ከተሞችን ሠራ፥ ብዙም የበግና የላም መንጋ ሰበሰበ።
30
ይህም ሕዝቅያስ የላይኛውን የግዮንን ውኃ ምንጭ ደፈነ፥ በዳዊትም ከተማ በምዕራብ በኩል አቅንቶ አወረደው። የሕዝቅያስም ሥራ ሁሉ ተከናወነ።
31
ነገር ግን የባቢሎን መሳፍንት መልእክተኞች በአገሩ ላይ ስለ ተደረገው ተአምራት ይጠይቁት ዘንድ ወደ እርሱ በተላኩ ጊዜ እግዚአብሔር ይፈትነውና በልቡ ያለውን ሁሉ ያውቅ ዘንድ ተወው።
32
የሕዝቅያስም የቀረው ነገር፥ ቸርነቱም፥ እነሆ፥ በአሞጽ ልጅ በነቢዩ በኢሳይያስ ራእይ በይሁዳና በእስራኤልም ነገሥታት መጽሐፍ ተጽፎአል።
33
ሕዝቅያስም ከአባቶቹ ጋር አንቀላፋ፥ በዳዊትም ልጆች መቃብር በላይኛው ክፍል ቀበሩት፤ በይሁዳና በኢየሩሳሌምም የሚኖሩ ሁሉ በሞቱ አከበሩት። ልጁም ምናሴ በእርሱ ፋንታ ነገሠ።2 ዜና መዋዕል 32:1
2 ዜና መዋዕል 32:2
2 ዜና መዋዕል 32:3
2 ዜና መዋዕል 32:4
2 ዜና መዋዕል 32:5
2 ዜና መዋዕል 32:6
2 ዜና መዋዕል 32:7
2 ዜና መዋዕል 32:8
2 ዜና መዋዕል 32:9
2 ዜና መዋዕል 32:10
2 ዜና መዋዕል 32:11
2 ዜና መዋዕል 32:12
2 ዜና መዋዕል 32:13
2 ዜና መዋዕል 32:14
2 ዜና መዋዕል 32:15
2 ዜና መዋዕል 32:16
2 ዜና መዋዕል 32:17
2 ዜና መዋዕል 32:18
2 ዜና መዋዕል 32:19
2 ዜና መዋዕል 32:20
2 ዜና መዋዕል 32:21
2 ዜና መዋዕል 32:22
2 ዜና መዋዕል 32:23
2 ዜና መዋዕል 32:24
2 ዜና መዋዕል 32:25
2 ዜና መዋዕል 32:26
2 ዜና መዋዕል 32:27
2 ዜና መዋዕል 32:28
2 ዜና መዋዕል 32:29
2 ዜና መዋዕል 32:30
2 ዜና መዋዕል 32:31
2 ዜና መዋዕል 32:32
2 ዜና መዋዕል 32:33


2 ዜና መዋዕል 1 / 2ዜና 1
2 ዜና መዋዕል 2 / 2ዜና 2
2 ዜና መዋዕል 3 / 2ዜና 3
2 ዜና መዋዕል 4 / 2ዜና 4
2 ዜና መዋዕል 5 / 2ዜና 5
2 ዜና መዋዕል 6 / 2ዜና 6
2 ዜና መዋዕል 7 / 2ዜና 7
2 ዜና መዋዕል 8 / 2ዜና 8
2 ዜና መዋዕል 9 / 2ዜና 9
2 ዜና መዋዕል 10 / 2ዜና 10
2 ዜና መዋዕል 11 / 2ዜና 11
2 ዜና መዋዕል 12 / 2ዜና 12
2 ዜና መዋዕል 13 / 2ዜና 13
2 ዜና መዋዕል 14 / 2ዜና 14
2 ዜና መዋዕል 15 / 2ዜና 15
2 ዜና መዋዕል 16 / 2ዜና 16
2 ዜና መዋዕል 17 / 2ዜና 17
2 ዜና መዋዕል 18 / 2ዜና 18
2 ዜና መዋዕል 19 / 2ዜና 19
2 ዜና መዋዕል 20 / 2ዜና 20
2 ዜና መዋዕል 21 / 2ዜና 21
2 ዜና መዋዕል 22 / 2ዜና 22
2 ዜና መዋዕል 23 / 2ዜና 23
2 ዜና መዋዕል 24 / 2ዜና 24
2 ዜና መዋዕል 25 / 2ዜና 25
2 ዜና መዋዕል 26 / 2ዜና 26
2 ዜና መዋዕል 27 / 2ዜና 27
2 ዜና መዋዕል 28 / 2ዜና 28
2 ዜና መዋዕል 29 / 2ዜና 29
2 ዜና መዋዕል 30 / 2ዜና 30
2 ዜና መዋዕል 31 / 2ዜና 31
2 ዜና መዋዕል 32 / 2ዜና 32
2 ዜና መዋዕል 33 / 2ዜና 33
2 ዜና መዋዕል 34 / 2ዜና 34
2 ዜና መዋዕል 35 / 2ዜና 35
2 ዜና መዋዕል 36 / 2ዜና 36