1 |
የእስራኤል ልጆች ከግብጽ ምድር ከወጡ አራት መቶ ሰማንያ ዓመት በሆነ ጊዜ፥ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፥ ዚፍ በሚባለው በሁለተኛው ወር የእግዚአብሔርን ቤት መሥራት ጀመረ። |
2 |
ንጉሡ ሰሎሞንም ለእግዚአብሔር የሠራው ቤት ርዝመቱ ስድሳ ክንድ፥ ወርዱም ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም ሠላሳ ክንድ ነበረ። |
3 |
በመቅደሱም ፊት ወለል ነበረ፤ ርዝመቱም እንደ መቅደሱ ወርድ ሀያ ክንድ፥ ወርዱም ከቤቱ ወደፊት አሥር ክንድ ነበረ። |
4 |
ለቤቱም በዓይነ ርግብ የተዘጉ መስኮቶች አደረገ። |
5 |
በቤቱም ግንብ ዙሪያ፥ በመቅደሱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግንብ ዙሪያ፥ ደርብ ሠራ፥ በዙሪያውም ጓዳዎች አደረገ። |
6 |
የታችኛውም ደርብ ወርዱ አምስት ክንድ፥ የመካከለኛው ደርብ ወርዱ ስድስት ክንድ፥ የሦስተኛውም ደርብ ወርዱ ሰባት ክንድ ነበረ። ሰረገሎቹ በቤቱ ግንብ ውስጥ እንዳይገቡ ከቤቱ ግንብ ውጭ ዓረፍቶች አደረገ። |
7 |
ቤቱም በተሠራ ጊዜ ፈጽመው በተወቀሩ ድንጋዮች ተሠራ፤ በተሠራም ጊዜ መራጃና መጥረቢያ የብረትም ዕቃ ሁሉ በቤቱ ውስጥ አልተሰማም። |
8 |
የታችኛውም ደርብ ጓዳዎች በር በቤቱ ቀኝ አጠገብ ነበረ። ከዚያም ወደ መካከለኛው ደርብ፥ ከመካከለኛውም ወደ ሦስተኛው ደርብ በመውጫ ያስወጣ ነበር። |
9 |
ቤቱንም ሠርቶ ፈጸመው፤ በዝግባው ሰረገሎችና ሳንቃዎች ከደነው። |
10 |
በቤቱም ሁሉ ዙሪያ ቁመታቸው አምስት አምስት ክንድ የሆነ ደርቦች ሠራ፤ ከቤቱም ጋር በዝግባ እንጨት አጋጠማቸው። |
11 |
የእግዚአብሔርም ቃል ወደ ሰሎሞን መጣ እንዲህ ሲል። |
12 |
ስለዚህ ስለምትሠራው ቤት በሥርዓቴ ብትሄድ፥ ፍርዴንም ብታደርግ፥ ትመላለስበትም ዘንድ ትእዛዜን ሁሉ ብትጠብቅ፥ ለአባትህ ለዳዊት የነገርሁትን ቃል ከአንተ ጋር አጸናለሁ። |
13 |
በእስራኤልም ልጆች መካከል እኖራለሁ፥ ሕዝቤንም እስራኤልን አልጥልም። |
14 |
ሰሎሞንም ቤቱን ሠራው፥ ፈጸመውም። |
15 |
የቤቱንም ግንብ ውስጡን በዝግባ ሳንቃ ለበጠ፤ ከቤቱም መሠረት ጀምሮ እስከ ጣራው ድረስ ውስጡን በእንጨት ለበጠው፤ ደግሞም የቤቱን ወለል በጥድ እንጨት ከደነው። |
16 |
በቤቱ ውስጥ ቅድስተ ቅዱሳን ይሆን ዘንድ ኋለኛውን ሀያውን ክንድ በዝግባ እንጨት ጋረደው። |
17 |
በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ያለውም መቅደስ ርዝመቱ አርባ ክንድ ነበረ። |
18 |
የቤቱንም ውስጥ በተጐበጐበና በፈነዳ አበባ በተቀረጸ ዝግባ ለበጠው፤ ሁሉም ዝግባ ነበረ፤ ድንጋዩም አልታየም ነበር። |
19 |
በዚያም የእግዚአብሔርን ቃል ኪዳን ታቦት ያኖር ዘንድ በቤቱ ውስጥ ቅድስተ ቅዱሳኑን አበጀ። |
20 |
የቅድስተ ቅዱሳንም ርዝመት ሀያ ክንድ፥ ስፋቱም ሀያ ክንድ፥ ቁመቱም ሀያ ክንድ ነበረ፤ በጥሩ ወርቅም ለበጠው። |
21 |
በቅድስተ ቅዱሳኑም ፊት ከዝግባ የተሠራ መሠዊያ አደረገ፤ በጥሩ ወርቅም ለበጠው። |
22 |
ቤቱንም ሁሉ ፈጽሞ በወርቅ ለበጠው፤ በቅድስተ ቅዱሳኑም ፊት የነበረውን መሠዊያ ሁሉ በወርቅ ለበጠው። |
23 |
በቅድስተ ቅዱሳኑም ውስጥ ቁመታቸው አሥር ክንድ የሆነ ከወይራ እንጨት ሁለት ኪሩቤል ሠራ። |
24 |
የኪሩብም አንደኛው ክንፍ አምስት ክንድ፥ የኪሩብም ሁለተኛው ክንፍ አምስት ክንድ ነበረ፤ ከአንደኛው ክንፍ ጫፍ ጀምሮ እስክ ሁለተኛው ክንፍ ጫፍ ድረስ አሥር ክንድ ነበረ። |
25 |
ሁለተኛውም ኪሩብ አሥር ክንድ ነበረ፤ ሁለቱም ኪሩቤል አንድ ልክና አንድ መልክ ነበረ። |
26 |
የአንዱ ኪሩብ ቁመት አሥር ክንድ ነበረ፥ የሁለተኛውም ኪሩብ እንዲሁ ነበረ። |
27 |
ኪሩቤልንም በውስጠኛው ቤት አኖራቸው፤ የኪሩቤልም ክንፎቻቸው ተዘርግተው ነበር፤ የአንዱም ኪሩብ ክንፍ አንደኛውን ግንብ ይነካ ነበር፥ የሁለተኛውም ኪሩብ ክንፍ ሁለተኛውን ግንብ ይነካ ነበር፤ የሁለቱም ክንፎች በቤቱ መካከል እርስ በርሳቸው ይነካኩ ነበር። |
28 |
ኪሩቤልንም በወርቅ ለበጣቸው። |
29 |
በቤቱም ግንብ ሁሉ ዙሪያ በውስጥና በውጭ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸ። |
30 |
የቤቱንም ወለል በውስጥና በውጭ በወርቅ ለበጠ። |
31 |
ለቅዱስተ ቅዱሳኑም መግቢያ ከወይራ እንጨት ደጆች ሠራ፤ መድረኩንና መቃኖቹን ደፉንም አምስት ማዕዘን አደረገ። |
32 |
ሁለቱንም ደጆች ከወይራ እንጨት ሠራ፤ የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፥ በወርቅም ለበጣቸው፤ ኪሩቤልናና የዘንባባውን ዛፍ በወርቅ ለበጣቸው። |
33 |
እንዲሁም ለመቅደሱ መግቢያ ከወይራ እንጨት አራት ማዕዘን መቃን አደረገ። |
34 |
ሁለቱንም ደጆች ከጥድ እንጨት ሠራ፤ አንዱ ደጅ በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ፥ ሁለተኛውም ደጅ በማጠፊያ ከተያያዘ ከሁለት ሳንቃ ተደረገ። |
35 |
የኪሩቤልንና የዘንባባ ዛፍ የፈነዳም አበባ ምስል ቀረጸባቸው፤ በተቀረጸውም ሥራ ላይ በወርቅ ለበጣቸው። |
36 |
የውስጠኛውንም አደባባይ ቅጥር ሦስቱን ተራ በተጠረበ ድንጋይ፥ አንዱንም ተራ በዝግባ ሳንቃ ሠራው። |
37 |
በአራተኛው ዓመት ዚፍ በሚባል ወር የእግዚአብሔር ቤት ተመሠረተ። |
38 |
በአሥራ አንደኛውም ዓመት ቡል በሚባል በስምንተኛው ወር ቤቱ እንደ ክፍሎቹና እንደ ሥርዓቱ ሁሉ ተጨረሰ። በሰባትም ዓመት ውስጥ ሠራው። a
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
1 ነገሥት 6:1 |
1 ነገሥት 6:2 |
1 ነገሥት 6:3 |
1 ነገሥት 6:4 |
1 ነገሥት 6:5 |
1 ነገሥት 6:6 |
1 ነገሥት 6:7 |
1 ነገሥት 6:8 |
1 ነገሥት 6:9 |
1 ነገሥት 6:10 |
1 ነገሥት 6:11 |
1 ነገሥት 6:12 |
1 ነገሥት 6:13 |
1 ነገሥት 6:14 |
1 ነገሥት 6:15 |
1 ነገሥት 6:16 |
1 ነገሥት 6:17 |
1 ነገሥት 6:18 |
1 ነገሥት 6:19 |
1 ነገሥት 6:20 |
1 ነገሥት 6:21 |
1 ነገሥት 6:22 |
1 ነገሥት 6:23 |
1 ነገሥት 6:24 |
1 ነገሥት 6:25 |
1 ነገሥት 6:26 |
1 ነገሥት 6:27 |
1 ነገሥት 6:28 |
1 ነገሥት 6:29 |
1 ነገሥት 6:30 |
1 ነገሥት 6:31 |
1 ነገሥት 6:32 |
1 ነገሥት 6:33 |
1 ነገሥት 6:34 |
1 ነገሥት 6:35 |
1 ነገሥት 6:36 |
1 ነገሥት 6:37 |
1 ነገሥት 6:38 |
|
|
|
|
|
|
1 ነገሥት 1 / 1ነገሥ 1 |
1 ነገሥት 2 / 1ነገሥ 2 |
1 ነገሥት 3 / 1ነገሥ 3 |
1 ነገሥት 4 / 1ነገሥ 4 |
1 ነገሥት 5 / 1ነገሥ 5 |
1 ነገሥት 6 / 1ነገሥ 6 |
1 ነገሥት 7 / 1ነገሥ 7 |
1 ነገሥት 8 / 1ነገሥ 8 |
1 ነገሥት 9 / 1ነገሥ 9 |
1 ነገሥት 10 / 1ነገሥ 10 |
1 ነገሥት 11 / 1ነገሥ 11 |
1 ነገሥት 12 / 1ነገሥ 12 |
1 ነገሥት 13 / 1ነገሥ 13 |
1 ነገሥት 14 / 1ነገሥ 14 |
1 ነገሥት 15 / 1ነገሥ 15 |
1 ነገሥት 16 / 1ነገሥ 16 |
1 ነገሥት 17 / 1ነገሥ 17 |
1 ነገሥት 18 / 1ነገሥ 18 |
1 ነገሥት 19 / 1ነገሥ 19 |
1 ነገሥት 20 / 1ነገሥ 20 |
1 ነገሥት 21 / 1ነገሥ 21 |
1 ነገሥት 22 / 1ነገሥ 22 |