1 |
ከሁለት ዓመት በኋላም ፈርዖን ሕልምን አየ፥ እነሆም፥ በወንዙ ዳር ቆሞ ነበር። |
2 |
እነሆም፥ መልካቸው ያማረ ሥጋቸውም የወፈረ ሰባት ላሞች ከወንዙ ወጡ፥ በውኃውም ዳር በመስኩ ይሰማሩ ነበር። |
3 |
ከእነርሱም በኋላ እነሆ መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ከወንዝ ወጡ፥ በእነዚያም ላሞች አጠገብ በወንዙ ዳር ይቆሙ ነበር። |
4 |
መልካቸው የከፋ ሥጋቸውም የከሳ እነዚያም ላሞች መልካቸው ያማረውን ሥጋቸው የወፈረውን ሰባቱን ላሞች ዋጡአቸው። ፈርዖንም ነቃ። |
5 |
ደግሞም ተኛ ሁለተኛም ሕልምን አየ። እነሆም በአንድ አገዳ ላይ የነበሩ ያማሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች ወጡ፤ |
6 |
እነሆም ከእነርሱ በኋላ የሰለቱና በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት እሸቶች ወጡ፤ |
7 |
የሰለቱትም እሸቶች ሰባቱን ያማሩና የዳበሩ እሸቶች ዋጡአቸው። |
8 |
ፈርዖንም ነቃ፥ እነሆም ሕልም ነበረ። በነጋም ጊዜ ነፍሱ ታወከችበት፤ ወደ ሕልም ተርጓሚዎች ሁሉ ወደ ግብፅ ጠቢባንም ሁሉ ልኮ ወደ እርሱ ጠራቸው፤ ፈርዖንም ሕልሙን ነገራቸው፥ ነገር ግን ከእነርሱ ለፈርዖን የሚተረጕም አልተገኘም። |
9 |
የዚያን ጊዜ የጠጅ አሳላፈዎቹ አለቃ እንዲህ ብሎ ለፈርዖን ተናገረ። እኔ ኃጢአቴን ዛሬ አስባለሁ፤ |
10 |
ፈርዖን በባሪይዎቹ ላይ ተቆጣ፥ እኔንም የእንጀራ አበዛዎቹንም አለቃ በግዞት ስፍራ በዘበኞች አለቃ ቤት አኖረን፤ |
11 |
እኛም በአንዲት ሌሊት ሕልምን አለምን፥ እኔና እርሱ፤ እያንዳንዳችን እንደ ሕልማችን ትርጓሜ አለምን። |
12 |
በዚያም የዘበኞቹ አለቃ ባሪያ የሆነ አንድ ዕብራዊ ጕልማሳ ከእኛ ጋር ነበረ፤ ለእርሱም ነገርነው፥ ሕልማችንንም ተረጐመልን፤ ለእያንዳንዱም እንደ ሕልሙ ተረጐመልን። |
13 |
እንዲህም ሆነ፤ እንደ ተረጐመልን እንደዚያው ሆነ፤ እኔ ወደ ሹመቴ ተመለስሁ፥ እርሱም ተሰቀለ። |
14 |
ፈርዖንም ልኮ ዮሴፍን አስጠራ፥ ከግዞት ቤትም አስቸኰሉት፤ እርሱም ተላጨ፥ ልብሱንም ለወጠ፥ ወደ ፈርዖንም ገባ። |
15 |
ፈርዖንም ዮሴፍን አለው። ሕልምን አየሁ፥ የሚተረጕመውም አልተገኘም፤ ሕልምን እንደ ሰማህ፥ እንደ ተረጐምህም ስለ አንተ ሰማሁ። |
16 |
ዮሴፍም ለፈርዖን እንዲህ ብሎ መለሰ። ይህ በእኔ አይደለም፤ እግዚአብሔር ግን ለፈርዖን በደኅንነት ይመልስለታል። |
17 |
ፈርዖንም ለዮሴፍ እንዲህ አለው። እነሆ፥ በሕልሜ በወንዝ ዳር ቆሜ ነበር፤ |
18 |
እነሆም፥ ሥጋቸው የወፈረ መልካቸውም ያማረ ሰባት ላሞች ወጡ፥ በመስኩም ይሰማሩ ነበር፤ |
19 |
ከእነርሱም በኋላ እነሆ የደከሙ መልካቸውም እጅግ የከፋ ሥጋቸውም የከሳ ሌሎች ሰባት ላሞች ወጡ፤ በግብፅም ምድር ሁሉ እንደ እነርሱ መልከ ክፉ ከቶ አላየሁም፤ |
20 |
የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ላሞች የመጀመሪያዎቹን ወፍራሞቹን ሰባት ላሞች ዋጡአቸው፥ |
21 |
በሆዳቸውም ተዋጡ፤ በሆዳቸውም እንደተዋጡ አልታወቀም፥ መልካቸውም በመጀመሪያ እንደ ነበረው የከፋ ነበረ። ነቃሁም። |
22 |
በሕልሜም እነሆ የዳበሩና መልካም የሆኑ ሰባት እሸቶች በአንድ አገዳ ሲወጡ አየሁ፤ |
23 |
ከእነርሱም በኋላ እነሆ የደረቁና የሰለቱ በምሥራቅ ነፋስ የተመቱ ሰባት እሸቶች ወጡ፤ |
24 |
የሰለቱት እሸቶች ያማሩትን ሰባቱን እሸቶች ዋጡአቸው። ለሕልም ተርጓሚዎችም ሕልሜን ነገርሁ የሚተረጕምልኝም አጣሁ። |
25 |
ዮሴፍም ፈርዖንን አለው። የፈርዖን ሕልሙ አንድ ነው፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን ነግሮታል። |
26 |
ሰባቱ መልካካሞች ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ ሰባቱም መልካካሞች እሸቶች ሰባት ዓመታት ናቸው፤ ሕልሙ አንድ ነው። |
27 |
ከእነርሱም በኋላ የወጡት የከሱትና መልከ ክፋዎቹ ሰባት ላሞች ሰባት ዓመታት ናቸው፥ የሰለቱትና የምሥራቅ ነፋስ የመታቸው ሰባቱም እሸቶች እነርሱ ራብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ናቸው። |
28 |
ለፈርዖን የነገርሁት ነገር ይህ ነው፤ እግዚአብሔር ሊያደርገው ያለውን ለፈርዖን አሳየው። |
29 |
እነሆ በግብፅ ምድር ሁሉ እጅግ ጥጋብ የሚሆንባቸው ሰባት ዓመታት ይመጣሉ፤ |
30 |
ደግሞ ከዚህ በኋላ የሰባት ዓመት ራብ ይመጣል፥ በግብፅ አገር የነበረውም ጥጋብ ሁሉ ይረሳል፤ ራብም ምድርን በጣም ያጠፋል፤ |
31 |
በኋላ ከሚሆነው ከዚያ ራብ የተነሣም በምድር የሆነው ጥጋብ አይታወቅም፥ እጅግ ጽኑ ይሆናልና። |
32 |
ሕልሙም ለፈርዖን ደጋግሞ መታየቱ ነገሩ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ስለ ሆነ ነው፥ እግዚአብሔርም ፈጥኖ ያደርገዋል። |
33 |
አሁንም ፈርዖን ብልህና አዋቂ ሰውን ይፈልግ፥ በግብፅ ምድር ላይም ይሹመው። |
34 |
ፈርዖን በምድር ላይ ሹማምትን ይሹም፤ በሰባቱም የጥጋብ ዓመታት ከሚገኘው ፍሬ በግብፅ ምድር ሁሉ ከአምስት እጅ አንደኛውን ይውሰድ። |
35 |
የሚመጡትን የመልካሞቹን ዓመታት እህላቸውን ያከማቹ፤ ስንዴውንም ከፈርዖን እጅ በታች ያኑሩ፥ እህሎችም በከተሞች ይጠበቁ። |
36 |
በግብፅ ምድር ስለሚሆነው ስለ ሰባቱ ዓመታት ራብ እህሉ ተጠብቆ ይኑር፥ ምድሪቱም በራብ አትጠፋም። |
37 |
ነገሩም በፈርዖንና በሎሌዎቹ ፊት መልካም ሆነ፤ |
38 |
ፈርዖንም ሎሌዎቹን እንዲህ አላቸው። በውኑ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበትን እንደዚህ ያለ ሰው እናገኛለንን? |
39 |
ፈርዖንም ዮሴፍን አለው። እንደ አንተ ያለ ብልህ አዋቂም ሰው የለም፥ እግዚአብሔር ይህን ሁሉ ገልጦልሃልና። |
40 |
አንተ በቤቴ ላይ ተሾም፥ ሕዝቤም ሁሉ ለቃልህ ይታዘዝ፤ እኔ በዙፋኔ ብቻ ከአንተ እበልጣለሁ። |
41 |
ፈርዖንም ዮሴፍን። በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ሾምሁህ አለው። |
42 |
ፈርዖን ቀለበቱን ከእጁ አወለቀ በዮሴፍ እጅም አደረገው፥ ነጭ የተልባ እግር ልብስንም አለበሰው፥ በአንገቱም የወርቅ ዝርግፍን አደረገለት፤ |
43 |
የእርሱም በምትሆን በሁለተኛይቱ ሰረገላ አስቀመጠው፥ አዋጅ ነጋሪም። ስገዱ እያለ በፊት በፊቱ ይጮኽ ነበር፤ እርሱም በግብፅ ምድር ሁሉ ላይ ተሾመ። |
44 |
ፈርዖንም ዮሴፍን አለው። እኔ ፈርዖን ነኝ፤ በግብፅ አገር ሁሉ ያለ አንተ ማንም እጁንም እግሩንም አያንሣ። |
45 |
ፈርዖንም የዮሴፍን ስም ጸፍናት ፐዕናህ ብሎ ጠራው፤ የሄልዮቱ ከተማ ካህን የDoጥፌራ ልጅ የምትሆን አስናትን አጋባው። ዮሴፍም በግብፅ ምድር ሁሉ ወጣ። |
46 |
ዮሴፍም በግብፅ ንጉሥ በፈርዖን ፊት በቆመ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዓመት ነበረ። ዮሴፍም ከፈርዖን ፊት ወጣ፥ የግብፅ ምድርንም ሁሉ ዞረ። |
47 |
በሰባቱም በጥጋብ ዓመታት የምድሪቱ ፍሬ ክምር ሆነ። |
48 |
በግብፅ ምድር ሁሉ ያለውን የሰባቱን ዓመት እህል ሁሉ ሰበሰበ፥ እህልንም በከተሞቹ አደለበ፤ በየከተማይቱ ዙሪያ ያለውን የእርሻውን እህል ሁሉ በዚያው ከተተ። |
49 |
ዮሴፍም እንደ ባሕር አሸዋ እጅግ ብዙ የሆነ ስንዴን አከማቸ፥ መስፈርን እስኪተው ድረስ፤ ሊሰፈር አልተቻለምና። |
50 |
ለዮሴፍም የሄልዮቱ ከተማ ካህን የDoጥፌራ ልጅ አስናት የወለደችለት ሁለት ልጆች የራብ ዘመን ገና ሳይመጣ ተወለዱለት። |
51 |
ዮሴፍም የበኵር ልጁን ስም ምናሴ ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል። እግዚአብሔር መከራዬን ሁሉ የአባቴንም ቤት አስረሳኝ፤ |
52 |
የሁለተኛውንም ስም ኤፍሬም ብሎ ጠራው፥ እንዲህ ሲል። እግዚአብሔር በመከራዬ አገር አፈራኝ። |
53 |
በግብፅ ምድር የነበረውም የሰባቱ ዓመት ጥጋብ አለፈ፥ |
54 |
ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ። |
55 |
የግብፅ ምድርም ሁሉ ተራበ፥ ሕዝቡም ስለ እህል ወደ ፈርዖን ጮኸ፤ ፈርዖንም የግብፅ ሰዎችን ሁሉ። ወደ ዮሴፍ ሂዱ፥ እርሱ ያላችሁንም ሁሉ አድርጉ አላቸው። |
56 |
በምድርም ሁሉ ላይ ራብ ሆነ፤ ዮሴፍም እህል ያለበትን ጎተራ ሁሉ ከፍቶ ለግብፅ ሰዎች ሁሉ ይሸጥ ነበር፤ ራብም በግብፅ ምድር ጸንቶ ነበር። |
57 |
አገሮችም ሁሉ እህል ይገዙ ዘንድ ወደ ግብፅ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ በምድር ሁሉ ራብ እጅግ ጸንቶ ነበርና።
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |
|
|
|
|
|
|
|
|
|
|
ዘፍጥረት 41:1 |
ዘፍጥረት 41:2 |
ዘፍጥረት 41:3 |
ዘፍጥረት 41:4 |
ዘፍጥረት 41:5 |
ዘፍጥረት 41:6 |
ዘፍጥረት 41:7 |
ዘፍጥረት 41:8 |
ዘፍጥረት 41:9 |
ዘፍጥረት 41:10 |
ዘፍጥረት 41:11 |
ዘፍጥረት 41:12 |
ዘፍጥረት 41:13 |
ዘፍጥረት 41:14 |
ዘፍጥረት 41:15 |
ዘፍጥረት 41:16 |
ዘፍጥረት 41:17 |
ዘፍጥረት 41:18 |
ዘፍጥረት 41:19 |
ዘፍጥረት 41:20 |
ዘፍጥረት 41:21 |
ዘፍጥረት 41:22 |
ዘፍጥረት 41:23 |
ዘፍጥረት 41:24 |
ዘፍጥረት 41:25 |
ዘፍጥረት 41:26 |
ዘፍጥረት 41:27 |
ዘፍጥረት 41:28 |
ዘፍጥረት 41:29 |
ዘፍጥረት 41:30 |
ዘፍጥረት 41:31 |
ዘፍጥረት 41:32 |
ዘፍጥረት 41:33 |
ዘፍጥረት 41:34 |
ዘፍጥረት 41:35 |
ዘፍጥረት 41:36 |
ዘፍጥረት 41:37 |
ዘፍጥረት 41:38 |
ዘፍጥረት 41:39 |
ዘፍጥረት 41:40 |
ዘፍጥረት 41:41 |
ዘፍጥረት 41:42 |
ዘፍጥረት 41:43 |
ዘፍጥረት 41:44 |
ዘፍጥረት 41:45 |
ዘፍጥረት 41:46 |
ዘፍጥረት 41:47 |
ዘፍጥረት 41:48 |
ዘፍጥረት 41:49 |
ዘፍጥረት 41:50 |
ዘፍጥረት 41:51 |
ዘፍጥረት 41:52 |
ዘፍጥረት 41:53 |
ዘፍጥረት 41:54 |
ዘፍጥረት 41:55 |
ዘፍጥረት 41:56 |
ዘፍጥረት 41:57 |
|
|
|
|
|
|
ዘፍጥረት 1 / ዘፍጥ 1 |
ዘፍጥረት 2 / ዘፍጥ 2 |
ዘፍጥረት 3 / ዘፍጥ 3 |
ዘፍጥረት 4 / ዘፍጥ 4 |
ዘፍጥረት 5 / ዘፍጥ 5 |
ዘፍጥረት 6 / ዘፍጥ 6 |
ዘፍጥረት 7 / ዘፍጥ 7 |
ዘፍጥረት 8 / ዘፍጥ 8 |
ዘፍጥረት 9 / ዘፍጥ 9 |
ዘፍጥረት 10 / ዘፍጥ 10 |
ዘፍጥረት 11 / ዘፍጥ 11 |
ዘፍጥረት 12 / ዘፍጥ 12 |
ዘፍጥረት 13 / ዘፍጥ 13 |
ዘፍጥረት 14 / ዘፍጥ 14 |
ዘፍጥረት 15 / ዘፍጥ 15 |
ዘፍጥረት 16 / ዘፍጥ 16 |
ዘፍጥረት 17 / ዘፍጥ 17 |
ዘፍጥረት 18 / ዘፍጥ 18 |
ዘፍጥረት 19 / ዘፍጥ 19 |
ዘፍጥረት 20 / ዘፍጥ 20 |
ዘፍጥረት 21 / ዘፍጥ 21 |
ዘፍጥረት 22 / ዘፍጥ 22 |
ዘፍጥረት 23 / ዘፍጥ 23 |
ዘፍጥረት 24 / ዘፍጥ 24 |
ዘፍጥረት 25 / ዘፍጥ 25 |
ዘፍጥረት 26 / ዘፍጥ 26 |
ዘፍጥረት 27 / ዘፍጥ 27 |
ዘፍጥረት 28 / ዘፍጥ 28 |
ዘፍጥረት 29 / ዘፍጥ 29 |
ዘፍጥረት 30 / ዘፍጥ 30 |
ዘፍጥረት 31 / ዘፍጥ 31 |
ዘፍጥረት 32 / ዘፍጥ 32 |
ዘፍጥረት 33 / ዘፍጥ 33 |
ዘፍጥረት 34 / ዘፍጥ 34 |
ዘፍጥረት 35 / ዘፍጥ 35 |
ዘፍጥረት 36 / ዘፍጥ 36 |
ዘፍጥረት 37 / ዘፍጥ 37 |
ዘፍጥረት 38 / ዘፍጥ 38 |
ዘፍጥረት 39 / ዘፍጥ 39 |
ዘፍጥረት 40 / ዘፍጥ 40 |
ዘፍጥረት 41 / ዘፍጥ 41 |
ዘፍጥረት 42 / ዘፍጥ 42 |
ዘፍጥረት 43 / ዘፍጥ 43 |
ዘፍጥረት 44 / ዘፍጥ 44 |
ዘፍጥረት 45 / ዘፍጥ 45 |
ዘፍጥረት 46 / ዘፍጥ 46 |
ዘፍጥረት 47 / ዘፍጥ 47 |
ዘፍጥረት 48 / ዘፍጥ 48 |
ዘፍጥረት 49 / ዘፍጥ 49 |
ዘፍጥረት 50 / ዘፍጥ 50 |