1 |
የኖኅ ልጆች የሴም የካም የያፌት ትውልድ ይህ ነው፤ ከጥፋት ውኃም በኋላ ልጆች ተወለዱላቸው። |
2 |
የያፌት ልጆች ጋሜር፥ ማጎግ፥ ማዴ፥ ያዋን፥ ይልሳ፥ ቶቤል፥ ሞሳሕ፥ ቴራስ ናቸው። |
3 |
የጋሜርም ልጆች አስከናዝ፥ ሪፋት፥ ቴርጋማ ናቸው። |
4 |
የያዋንም ልጆች ኤሊሳ፥ ተርሴስ፥ ኪቲም፥ ሮድኢ ናቸው። |
5 |
ከእነዚህም የአሕዛብ ደሴቶች ሁሉ በየምድራቸው በየቋንቋቸው በየነገዳቸው በየሕዝባቸው ተከፋፈሉ። |
6 |
የካምም ልጆች ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ፥ ከነዓን ናቸው። |
7 |
የኩሽም ልጆች ሳባ፥ ኤውላጥ፥ ሰብታ፥ ራዕማ፥ ሰበቃታ ናቸው። የራዕማ ልጆችም ሳባ፥ ድዳን ናቸው። |
8 |
ኩሽም ናምሩድን ወለደ፤ እርሱም በምድር ላይ ኃያል መሆንን ጀመረ። |
9 |
እርሱም በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ ነበረ፤ ስለዚህም። በእግዚአብሔር ፊት ኃያል አዳኝ እንደ ናምሩድ ተባለ። |
10 |
የግዛቱም መጀመሪያ በሰናዖር አገር ባቢሎን፥ ኦሬክ፥ አርካድ፥ ካልኔ ናቸው። |
11 |
አሦርም ከዚያች አገር ወጣ፤ ነነዌን፥ የረሆቦትን ከተማ፥ ካለህን፥ |
12 |
በነነዌና በካለህ መካከልም ሬሴንን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት። |
13 |
ምጽራይምም ሉዲምን፥ ዐናሚምን፥ ላህቢምን፥ ነፍታሌምን፥ ፈትሩሲምን፥ |
14 |
ከእነርሱ የፍልስጥኤም ሰዎች የወጡባቸውን ከስሉሂምን፥ ቀፍቶሪምንም ወለደ። |
15 |
ከነዓንም የበኵር ልጁን ሲዶንን፥ ኬጢያውያንንም፥ |
16 |
ኢያቡሳውያንንም፥ አሞራውያንንም፥ |
17 |
ጌርጌሳውያንንም፥ ኤዊያውያንንም፥ |
18 |
ዐሩኬዎንንም፥ ሲኒንም፥ አራዴዎንንም፥ ሰማሪዎንንም፥ አማቲንም ወለደ። ከዚህም በኋላ የከነዓናውያን ነገድ ተበተኑ። |
19 |
የከነዓናውያንም ወሰን ከሲዶን አንሥቶ ወደ ጌራራ በኩል ሲል እስከ ጋዛ ድረስ ነው፤ ወደ ሰዶምና ወደ ገሞራ፥ ወደ አዳማና ወደ ሰቦይም በኩልም ሲል እስከ ላሣ ድረስ ነው። |
20 |
የካም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራችውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። |
21 |
ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፤ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ አባት የሆነ ነው። |
22 |
የሴምም ልጆች ኤላም፥ አሦር፥ አርፋክስድ፥ ሉድ፥ አራም ናቸው። |
23 |
የአራምም ልጆች ዑፅ፥ ሁል፥ ጌቴር፥ ሞሶሕ ናቸው። |
24 |
አርፋክስድም ቃይንምን ወለደ፤ ቃይንምም ሳላን፥ ሳላም ዔቦርን ወለደ። |
25 |
ለዔቦርም ሁለት ልጆች ተወለዱለት፤ የአንደኛው ስሙ ፋሌቅ ነው፥ ምድር በዘመኑ ተከፍላለችና፤ የወንድሙም ስም ዮቅጣን ነው። |
26 |
ዮቅጣንም ኤልሞዳድን፥ ሣሌፍንም፥ ሐስረሞትንም፥ |
27 |
ያራሕንም፥ ሀዶራምንም፥ አውዛልንም፥ |
28 |
ደቅላንም፥ ዖባልንም፥ አቢማኤልንም፥ |
29 |
ሳባንም፥ ኦፊርንም፥ ኤውላጥንም፥ ዩባብንም ወለደ፤ እነዚህ ሁሉ የዮቅጣን ልጆች ናቸው። |
30 |
ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው። |
31 |
የሴም ልጆች በየነገዳቸውና በየቋንቋቸው፥ በየምድራቸውና በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። |
32 |
የኖኅ የልጆቹ ነገዶች እንደ ትውልዳቸው በየሕዝባቸው እነዚህ ናቸው። አሕዛብም ከጥፋት ውኃ በኋላ በምድር ላይ ከእነዚህ ተከፋፈሉ። a
|
Amharic Bible (Selassie) 1962 |
Selassie 1962: © United Bible Societies 1962 |